🚨አጫጭር መረጃዎች

👉የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት በእየሩሳሌም የቀድሞ የእስራኤል ሴሚናሪ መምህር የነበረው አሮን ራማቲ 30 ሴቶችን እና ታዳጊዎችን በባርነት መያዙን ማመኑን ተከትሎ ለተጎጂዎቹ የማህበረሰብ አገልግሎት እና የገንዘብ ካሳ እንዲከፍል ተወስኖበታል ብለዋል።

👉ሮይተርስ፡ የባይደን አስተዳደር ሩሲያ በዩክሬን የምታደርገውን ጦርነት ደግፈዋል በሚል ንብረትነታቸው የሩሲያ፣ ቻይና፣ ቱርክ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ኪርጊስታን፣ ህንድ እና ደቡብ ኮሪያ የሆኑ 93 ተቋማት ላይ አዲስ የንግድ ማእቀብ ጥሏል።

👉ዋሽንግተን ታይምስ፡ ኢራን 5 የአቶሚክ ቦምቦችን ገንብታ ብትጨርስም ይፋ አላደረገችውም ምክንያቱም በአጭር ጊዜ ውስጥ ቁጥራቸውን ወደ 12 ማሳደግ አስባለች ብሏል፡፡

👉ኢራን፡ በቅርቡ በኢራን ደቡብ ምስራቅ የሽብር ጥቃት ዋና ፈፃሚ ከሆነው የጃይሽ አል-አድል አሸባሪ ቡድን መሪዎች አንዱ የሆነው ኢስማኤል ሻባክሽ በፓኪስታን ውስጥ በኢራን የጸጥታ ሃይሎች ከጥቂት ሰአታት በፊት ተገድሏል።

👉አሜሪካ፡ ሲ ኤን ኤን የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው የጆ ባይደን መንግስት የመን በቀይ ባህር መርከቦች ላይ የምታደርሰውን ጥቃት ለማስቆም ችግር ገጥሞታል ያለ ሲሆን የፔንታጎን ምክትል ቃል አቀባይ "ሁቲዎች ትልቅ የጦር መሳሪያ እንዳላቸው እናውቃለን። በጣም አቅም ያላቸው ናቸው። የላቀ የጦር መሳሪያ አላቸው፤ ምክንያቱም በየጊዜው ከኢራን የጦር መሳሪያ እያገኙ ነው" ብለዋል፡፡

ዘገባው እንደሚለው የአሜሪካ ባለስልጣናት በየመን ላይ የሚደርሰውን ጫና ለመጨመር መንገድ ለመፈለግ እየሞከሩ ነው; ምክንያቱም አንዳንድ የባይደን አስተዳደር ውስጥ ያሉ ኃላፊዎች የኃይል እርምጃ ብቻውን አይሰራም ይላሉ። እነዚህ ሰዎች በየመን ላይ የሚደርሰው ወታደራዊ ጫና በጣም አክሳሪ ግን ውጤታማ ያልሆነ ነው እንዲሁም ብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚገመቱ ሚሳኤሎችን ውድ ላልሆኑ ድሮኖች እና ሚሳኤሎች ማባከንን ይጠይቃል ወደሚል ድምዳሜ ደርሰዋል።

አንዳንድ የቀድሞ የአሜሪካ ባለስልጣናት የዋይት ሀውስ አቀራረብ እስካሁን በጣም ወግ አጥባቂ ነው እናም የባይደን መንግስት የጦር መሳሪያ መጋዘኖችን ከማጥቃት ይልቅ በየመን መሪዎች ላይ ማነጣጠር አስፈላጊ ነው ብለው ያምናሉ። የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን ስለየመን አንሳሩላህ ሲናገሩ “እኛን እያስደነቁን ቀጥለዋል። አሁንም ሌላ ምን እንዳላቸው እውቀቱ የለንም” ብለዋል።

👉የውጭ መገናኛ ብዙሃን፡- ሶስት ትንንሽ ጀልባዎች በኦማን ከሚገኘው "ካልሃት" ነዳጅ ማምረቻ በስተምስራቅ 175 ኖቲካል ማይል ርቀት ላይ ወደ አንድ ትልቅ መርከብ እየጠጉ ነው ሲሉ ሪፖርት አድርገዋል።

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group