Translation is not possible.

🚨 አጫጭር መረጃዎች፡-

ግብፅ፡- የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ ኤል ሲሲ ሀገራቸው ፍልስጤማውያንን ወደ ግብፅ በማናቸውም መንገድ ወይም መልኩ መፈናቀላቸውን ሙሉ በሙሉ አለማቀፋዊ መግባባት ባለበት አቋም መሰረት ውድቅ እንዳደረገች አረጋግጠዋል።

ሳዑዲ አረቢያ፡ የሳውዲ አረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፋይሰል ቢን ፋርሃን ❝ከእስራኤል ጋር ምንም ግንኙነት የለንም። ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ በጋዛ ያለውን ሰብአዊ ሁኔታ መፍታት ነው ያሉ ሲሆን ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመመስረት ነፃ የፍልስጤም ሀገረ መንግስት ምስራታ መረጋገጡ 'ቅድመ ሁኔታ' ነው ብለዋል።

ካናዳ፡- እስራኤል በራፋህ ልትወስደው ያቀደችው የምድር ጥቃት ፍልስጤማውያን መሄጃ ስለሌላቸው 'ተቀባይነት የለውም' ሲሉ የካናዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜላኒ ጆሊ ተናግረዋል።

እስራኤል፡- የእስራኤል ተቃዋሚ መሪ ያየር ላፒድ የረመዳን ወር ከመግባቱ በፊት የቀኝ አክራሪው የብሄራዊ ደህንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤን-ጊቪር ሥልጣናቸውን እንዲለቁ ጠይቀዋል። ላፒድ ይህን ያሉት ሰውየው በረመዳን ሙስሊሞች ወደ አል አቅሳ ምሰጂድ እንዳይገቡ የሚከለክል ህግ በማውጣታቸው ረመዳን ላይ በፍልስጤማዊያን እን የእስኤል የፀጥታ ኃይሎች መካከል ከፍተኛ ግጭት ይፈጠራል ብለው በመስጋት ነው፡፡

ሐማስ፡- የሐማስ መሪ ኢስማኤል ሃኒዬህ ከግብፅ ባለስልጣናት ጋር በጋዛ ላይ በቀጠለው የእስራኤል ጦርነት እና የእስረኞች ልውውጥ እንዲሁም በተኩስ አቁም ሀሳብ ላይ ለመምከር ካይሮ ገብተዋል ብሏል።

ኳታር፡- የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መጂድ አል አንሳሪ በጋዛ የተኩስ አቁም ንግግር እና በሃማስ እና በእስራኤል መካከል የእስረኞች ልውውጥ ዙሪያ ብዙ ልዩነቶች ቢኖሩመ ንግግሩ አሁንም ቀጥሏል ብለዋል፡፡

እስራኤል፡- የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ እስራኤል አላማዋን ከማሳካቷ በፊት በጋዛ ላይ የሚደረገውን ጦርነት ለማስቆም ለማንኛውንም የሀገር ውስጥም ሆነ የአለም አቀፍ ጫና እጅ እንደማትሰጥ ተናግራዋል።

እስራኤል፡- የእስራኤሉ የገንዘብ ሚኒስትር ቤዛሌል ስሞትሪች፡ "በምንም አይነት መስዋእትነት ምርኮኞቹን ከማስመለስ በላይ ሃማስን ጥፋት ቅድሚያ የምንሰጠው ነው ሲሉ ተናግረዋል። ይህም እስረኞችን በስምምነት ካልሆነ ማግኘት እንደማይችሉ ማመናቸውን ያሳያል እየተባለ ነው፡፡"

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group