Translation is not possible.

ዝም ስትሉ "ለምን ዝም አሉ?" ባዩ ብዙ ነው :: ስታወሩ "ብቻችንን እናውራ አሉ!" ባዩ ብዙ ነው :: ጨፍረር ብለህ ስትወጣ "ኧረ ፏ በል!" ያለህ አምሮብህ ሲያይህ "ማሻ አላህ!" በማለት ፋንታ "ልታይ ልታይ አበዛሳ!" ሲልህ ታገኘዋለህ :: ስትቀመጥ ተነስ ስትቆም ተቀመጥ ባዩ ብዙ ነው :: ስትተኛ ቀስቃሽ ስትነቃ አስተኚውም የትዬሌለ ነው ::

  ብቻ የትም ሁን የት ከአንተ ላይ ጥቁር ነጥብን ማውጣት የማይታክታቸው ብዙ ሰዎች ያጋጥሙሃል :: ሁሉም ሰው ሊወድህ አይችልምና ጠልተውህ ሊሆን ይችላል :: ሁሉም ሰው በሀሳብህ ሊስማማ አይችልምና ከሀሳብህ ተቃርኖ ውስጥ ገብተው ሊሆን ይችላል ::

   ስለዚህ ገንቢ ሀሳቦችን እየወሰድክ ከእውነት ጋር ባለመታከት ተጓዝ :: "ሌቷ እንደ ቀን ብርሃናማ በሆነ መንገድ ላይ ትቻችሗለሁ!" ብለዋልና እርሱን ያዝ :: ትኩረትህን በስራህ ላይ አድርግ ::

  መልካም ቀን

Send as a message
Share on my page
Share in the group