Translation is not possible.

ወላሂ አውፍ ብያለሁ‼

===============

✍ ዛሬ ኮልፌ መቃብር ተገኝቻለሁ። በቀብር ስነስርዓት ላይ ነውና የተገኘሁት አስቀብረን ስንመለስ አንድ አባት እንባ እየተናነቃቸው የሚያውቁትን ሰው ስም እየጠሩ ይጮሀሉ። አይናቸው ያረፈው እግርጌያቸው ያለው ቀብር ላይ ነው። ቀብሩ ላይ ለስም መፃፊያ በቆመው ድንጋይ ላይ  የሟች ስምና የተቀበረበት ቀን ተጽፎአል።

"ወይኔ ሱሌ፣ ወይኔ ሱሌ እኔ የት ጠፋህብኝ እላለሁ ለካ አንተ እዚህ ነህ? ወላሂ ወላሂ አውፍ ብዬ አለው!" እንባቸው እርግፍ ማለት ጀመረ።

"ወይኔ ሱሌ!" ይላሉ ደጋግመው።

አብሮኝ የነበረው ሱልጣን ወደ እሳቸው ጠጋ ብሎ "የሚያውቁት ቤተሰብ ነው?" ሲል ጠየቃቸው።

"በሥራ አጋጣሚ ነበር የምንተዋወቀው 160 ሺህ ብር አበድሬው ነበር። ለረጅም ጊዜ ጠፋብኝ ደውዬም ማግኝት አልቻልኩም፣ ብድር የወሰደበትን መዝገብ አልፎ አልፎ እየተመለከትኩና ስሙን ከነአያቱ እየጠራሁ የት ገባ እላለሁ?  ወይኔ ወንድሜ ለካ እዚህ መጥቶ ነው? ወይኔ ሱሌ ሁሉን ነገር ይቅር ብያለሁ።"

የሰውየው ሁኔታ ሟች የእሳቸው እድ ሳይከፈል በመሞቱ ሲሰቃይ እያዩ ለማስጣል የሚማጠኑ ይመስላሉ "ወላሂ አውፍ ብዬዋለሁ! ወላሂ አውፍ ብዬአለሁ ! " አሉ ደጋግመው።

ጎናቸው የቆመው ሱልጣን አይኑ እንባ አቀረረ። ሁላችንም በሁኔታቸው ስሜታችን ተነክቷል።

ባለቤትሽ ገንዘቤን ሳይሰጠኝ ሞተ ብሎ እናቴን በሐሰት የከሰታትንና የአባቴን ንብረት በሐራጅ ሊያሸጥ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደረሶ በኋላ አባቴ የከፈለበት ማስረጃ ተገኝቶ ጎዳና ላይ ከመውጣት የተረፍንበት አጋጣሚ ለቅፅበት ታወሰኝ።

የእኚህ ሰው ሁኔታ ደግሞ ፍፁም የተለየ ነው። እንባዬ የአይኔን በር አልፎ ለመውጣት እየተጋለ ነው።

ይባስ ብለው "ያለ አባት የቀሩት ልጆቹ በምን ሁኔታ ይሆን ያሉት? ያሉበትን አፈላልጌ እጠይቃቸዋለሁ ኢንሻአላህ!" ቁጢጥ ብለው ከተቀመጡበት ብድግ አሉ።

ሱልጣን በተቀመጡበት ረስተውት የተነሱትን የመኪናቸውን ቁልፍ አንስቶ ሰጣቸው።

ከዚያ ሰላማዊና ምንም መሆናችን ከሚያስታውሰን

የሙታን ስፍራ ስለ ነገ ሞታችን እያሰብን ወጣን።

እንዲህም አይነት ሰው አለ።»

©: ጀማል አሕመድ

Send as a message
Share on my page
Share in the group