Terjemahan tidak mungkin.

*★ መውደድ ሚወዱትን በመከተል ነው !*

* አዎ የምትወደውን ሰው ከኋላኋላው ትከተለዋለህ ፣ በአስተሳሰቡም ፣ በንግግሩም፣ በተግባሩም እሱን ለመምሰል ትጥራለህ እንጂ ከሱ ለመቅደምም ሆነ ለመቃረን በፉፁም አታስብም ። በነብዩ ሷለላሁ አለይሂ ዘመን የነበሩ ሙሽሪኮች እኛኮ አላህን እንወዳለን ሲሉ አላህ የውዴታ መፈተኛ የሆነውን ይህን የቁርኣን አንቀጽ አወረደ :—

{قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ اللَّهَ فَاتَّبِعُونِي يُحْبِبْكُمُ اللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ }(ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 31)

* ((በላቸው፡- «አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፡፡ ኀጢኣቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡»))

★አዎ አላህን መውደድ በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባርም መሆን አለበት ለዚህም ማረጋገጫው ነብዩ ሙሀመድን ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም መከተል ነው ። በዚሁ ልክ የነብዩ ሙሀመድንም ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም ውዴታ ማረጋገጫው ሱናቸውን በመከተል ነው የሰሩትን በመስራት የተውትን በመተው ፣ ያዘዙትን በመታዘዝ የከለከሉትን በመከልከል ።

★ ያ አላህ እንወድሃለን ውዴታህን በተግባር ከሚያሳዩህ ባርያዎችህ አድርገን

★ ያ አላህ ውዱን ነብይህን ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም እንወዳለን ውዴታችንን በተግባር ከሚያውሉ ባርያዎችህ አድርገን 🤲🏻🤲🏻🤲🏻አሚን

Hantar sebagai mesej
Kongsi di halaman saya
Kongsi dalam kumpulan