Translation is not possible.

ቀጣዩ ምእራፍ አሸናፊውን የስነ-ሕንፃ ንድፍ (ፕላን) በተቻለ ፍጥነት አስፀድቆ ወደ ግንባታ መግባት ነው!!!

የታላቁ የንጉስ ነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ የኪነ-ህንፃ ቅድመ ንድፍ ውድድርን ATM ዲዛይነር ፒኤልሲ አሸነፈ!

ATM ዲዛይነር ፒኤልሲ ከአስር ተወዳዳሪዎች መካከል አንደኛ በማውጣት የአንድ ሚሊየን ሁለት መቶ ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል።

*****

የንጉስ ነጃሺ አብይ ኮሚቴ በኡስታዝ አቡበከር አህመድ ሰብሳቢነት እና በዶክተር ዓዲል ዘከሪያ ም/ሰብሳቢነት እንዲሁም በኢጂነር አንዋር ሱልጣን ዋና ፀሐፊነት ከተዋቀረበት ጊዜ ጀምሮ:የቴክኒክ ንኡስ ኮሚቴ በማቋቋምና ውድድሩን የሚዳኙ በዓለም አቀፍ ደረጃ ፕሮፌሺናል የሆኑ ዳኞችን በመመደብ በዛሬው እለት በእስተይ ሴቭ ሆቴል በተካሄደው አሸናፊውን የማብሰሪያ ውድድር ቀን እንዲደርስ እና በስኬት እንዲጠናቀቅ ለማድረግ ኃላፊነቱን ተወጥቷል።

*****

በቀጣይ አብይ ኮሚቴው አሸናፊውን ዲዛይን ለፕላን ኮሚሽን በማቅረብ አስፅድቆ በፍጥነት ወደ ግንባታው መግባት የሚጠበቀው ወሳኝ እርምጃ ይሆናል።

image
image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group