Translation is not possible.

      አንተና ሞት⚫️

⚫️ልክ ስትሞት ከሁሉም ቀድሞ ከአንተ የሚወገደው ስምህ ነው።

  እንደ ሞትክ "ሬሳው የታለ" ማለት ይጀምራሉ።

  ሊሰግዱብህ ሲፈልጉም

"ሰላተል ጀናዛ (የሬሳ ሰላት) ይሰገድ" ይባባላሉ።

ሊቀብሩህ ሲፈልጉም

  "ሬሳው አቅርቡት ይባባላሉ።"

👇

👉ገና ከጅረምሩ ካንተ ላይ ስምህ ይነሳል።

🚫ጎሳህ ብሄርህ ዘርህ አያታልልህ።

💫እቺ ዱንያ እንዴት የተዋረደችና የምንሄድባት ሀገር እንዴት የከበደች ናት?!

ተመልከት……

   ስትሞት ሦስት ዐይነት ሰዎች መርዶህ ይሰማሉ።

1ኛ,  በዘፈቀደ አንተን የሚያውቁህ ናቸው። መሞትህ ሲሰሙ

  "ውይ፣ ምስኪን ነበር፣ ሲያሳዝን" ይላሉ።

2ኛ, የሚቀርቡህ ጓደኛችህ ናቸው። በምትሞት ጊዜ

ለቀናት ወይም ለሳምንታት ሊያዝኑ ይችላሉ;  ከዝያ በኋላ ወደ ጉዳያቸውና ወደ ሳቃቸው ይመለሳሉ።

3ኛ, ቤትህ ውስጥ የሚፈጠረው ጥልቅ የሆነ ሀዘን ነው።

  እነርሱም ለሳምንታትና ለወራት አንዳንዴም ለዐመታት ሊያዝኑ ይችላሉ።

ከዝያም ወደ ቀጣይ ሕይወታቸውና ወደ ሳቃቸው መመለሳቸው አይቀርም።

☝እንዲህ ☝እንዲህ እያለ ዱንያ ላይ የነበረህ ታሪክህ ያከትማል።

💎የአኼራ ሕይወትህ ይጀምራል!!

🌙ቁንጅናህ

    🌙ንብረትህ

       🌙ጤንነትህ

          🌙ወላጆችህ

             🌙ልጆችህ

               🌙ባለቤትህ

      ሁሉ ካንተ ይወገዳሉ።

💎እውነተኛ የሆነው ሕይወት አሁን ትጀምራለህ።

💫ትጠየቃለህ………

    👉ጌታህ ማን ነው?

       👉ነብይህ ማን ነው?

         👉እምነትህ ምንድን ነው?

ምን ያህል ተዘጋጅተሃል??

Send as a message
Share on my page
Share in the group