Translation is not possible.

አፍቅሬ ተከዳሁ፣ አምኜ ተገፋሁ፣ ተስፋ አርጌ አጣሁ አትበል፡፡ ከሷ/ከሱ ከምትጣበቅ/ቂ ከአላህ ተጣበቅ፡፡ ተወኝ፣ ረሳኝ፣ ጣለኝ… አትበሉ፡፡ አላህ ብቻ አይጣላችሁ፡፡ እሱ ካልጣለን ዓለም ሁሉ ቢጥለን ምንም አንሆንም።ከሰው ሳይሆን ከአላህ ብዙ ጠብቁ፡፡ ከፈጠራችሁ እንጂ ከሰው ብዙ ተስፋ አታድርጉ፡፡

አላህ ከሰውም ከሀብትም ብዙ ብዙ አለው፡፡ ስለዚህ ከሱ ተስፋ አትቁረጡ፡፡ ሀሳባችሁ መስመር በሳተ ቁጥር ተመለሱ፣ በደከማችሁ ቁጥር ትጉ፣ በወደቃችሁ ቁጥር ተነሱ፡፡ ምኞታችሁ አልሰምር ብሎ እየራቀ በሄደ ልክ አንሰራሩ፡፡ በተስፋ መቁረጥ መቃብር ላይ ነፍስ ዝሩ፡፡ የሞተ የሚባለው ተስፋው የሞተ ነውና አትሙቱ፡፡ አታስቡ አትጨነቁ…

ከአላህ ጋር ከሆናችሁ የሚከብዳችሁ ነገር አይኖርም። የትኛውንም መሰናክል ታልፋላችሁ፣ ከጌታችሁ ጋር ሆናችሁ የማታልፉት መከራ አይኖርም፤ የትኛውንም መሰናከል ትሻገራላችሁ፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group