Translation is not possible.

ሰሞኑን ምን እየተካሄደ ነው⁉️

===================

✍ በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች "ፋኖ" ነን የሚሉ ቡድኖች የአማራ ክልልን ህዝብ ነፃ እናወጣለን በሚል ሽፋን የክልሉን ሙስሊም ማኅበረሰብ እያሰቃዩት ይገኛል።

በባህር ዳር ከተማና አካባቢዋ ብዙዎች እየታገቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር እየተጠየቁ ቆይተዋል። በሌሎችም የክልሉ አካባቢዎች ተመሳሳይ ነገር እየተስተዋለ ነው።

ከነዚህ ቡድኖች ባሻገር በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የሚገኙ የአሕባሽ ቡድኖች ከነዚህ ፋኖ ነን ከሚሉና አንዳንድ ሆድ አድ አደር የመንግስት አመራሮች ጋር በመሆን «ውሃብያ» የሚሉትን ሙስሊም ማኅበረሰብ እያሰቃዩ ይገኛሉ። በዳውንት ወረዳ የወረዳው አመራሮች ከነዚህ ጽንፈኞች ጋር በማበር በህጋዊ መንገድ የተመረጠውን መጅሊስ በመፈንቀል ህዝበ ሙስሊሙን ደም ሊያቃቡት ጫፍ ደርሰዋል።

እንደ ጃዊ ባሉ የክልሉ አካባቢዎች ከታች የምትመለከቱት አይነት አደገኛና መርዘኛ መልዕክት እየተሰራጨ ነው። ከዚህ መልዕክት ቀጥሎ የሚፈጠረውን በላእ አላህ ይወቅ።

በቤኒሻንጉል ክልል 43 አመታት ገደማ የቆየ መስጅድና መድረሳ መሬቱ እየተሸረሸረ ለቤተ ክርስቲያንና ለግለሰቦች መኖሪያ ይሆን ዘንድ መሰጠቱን ሰምተናል። ይህ ጉዳይ በቪድዮም ቀርቧል። https://t.me/MuradTadesse/33710

ከተወሰኑ ወራቶች ወዲህ ትንሽ ተንፈስ ብለን ነበር። አሁን ደግሞ በማናውቀው ጉዳይ ምን በላእ አምጥተው ሊያንጫጩን ይሆን? ምንስ እየተደገሰልን ይሆን?

አላህ በየቦታው ያሉ ንጹሐን ወገኖቻችንን ይጠብቅልን።

የአማራ ክልል መጅሊስ ከፌዴራሉ መጅሊስ፣ ከክልሉ አማራርና በየደረጃው ከሚመለከተው አካል ጋር እየተነጋገረ የክልሉን ሙስሊም ማኅበረሰብ ደህንነት ሊያስጠብቅ ይገባል። ደምፃቸው ታፍኖ ሲሰቃዩ ዝምታን መምረጥ የለብንም።

||

t.me/MuradTadesse

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group