Çeviri imkansız.

አቢሲንያ ባንክ እና እስልምና!

በንፅፅር ዳዕዋ ዘርፍ ላይ የምናውቀውን ኡስታዝ ሙሐመድ ከድር ትላንት ዓለም ገና አካባቢ አቢሲኒያ ባንክ አጠገብ ያደረገውን ዳዕዋ ቪድዮውን ተመልክተናል። አንድ የባንኩ ሠራተኛ ኡስታዙን ከዳዕዋው ለማስቆምና ማይኩን እዘጋለሁ ብሎ ሲታገል ይታያል።

ይህ'ኔ እዛው ባንክ ውስጥ የርሱ ቢሮ ላይ የማሪያምና የእየሱስ ስዕል የሚሉትን ለጥፎ ሊገኝ ይችላል፤ ወይንም የሆነ ከበዓላቸው ጋር የተያያዘ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ወይም የሆነ የነርሱው ኃይማኖታዊ ጥቅስ ሊገኝ ይችላል። በጣም የሚገርመኝ ነገር ሌላውን ይተውና የሙስሊሙ ጊዜ ጥላቻቸውን በሴኪዩላሪዝም ሽፋን ህግ ለመተግበር ሲፍጨረጨሩ ይታያሉ።

ባንኩ የእምነት መስበኪያ አይደለም ብሎ የማይገናኘውን ለማገናኘት ሞከረ እንጂ ይህ'ኔ ባንኩ ራሱ ለቤተ ክርስቲያን አስራት ይከፍል ይሆናል፤ ወይንም የሆነ ውስጣዊ መዋጮና ድጋፍ ላይ ይሳተፍ ይሆናል እንደውም የተረጋገጠ መረጃ ባይኖርም ከባንኩ ሰዎች እንደሰማሁት ባንኩ ከትርፉ ላይ 3-5% ለቤተ-ክርስቲያን ይደጉማል።

ከባንኩ በብዛት ርቀት ላይ እየተካሄደ የነበረን ዳዕዋ ይረብሻል ብሎ ለማስቆም መሞከር ነውር ነው ይህኔ ጴንጤ ቢሆን ማንም አይናገረውም። በነበረው ነገር አፍረናል። አቢሲኒያ ባንክ በተለይም የዚያ ቅርንጫፍ ኃላፊ ኡስታዙና ታዳሚውን ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል።

ኡስታዝ ሙሐመድ ከድር ደግሞ ሐቅም ስለነበረው ማይኩን አትዘጋም ብሎ ያስቆመበት መንገድም ተገቢ ነው

በንፅፅር ላይ የተሰማራችሁ ወንድሞች ጀግና ናችሁ በርቱ፤ ከመልካም ጸባይ ጋር የእስልምናን ውበት አሳዩ።

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

3 görüntüleme
Mesaj olarak gönder
Sayfamda paylaş
Grupta paylaş