Translation is not possible.

በንፅፅር ዳዕዋ ዘርፍ ላይ የምናውቀውን የኡስታዝ ሙሐመድ ኸዽርን ይህን ትናንት ዓለም ገና አካባቢ አቢሲኒያ ባንክ አጠገብ ያደረገውን ዳዕዋ ቪድዮውን እያየሁት ነበር።

አንድ የባንኩ ሠራተኛ ኡስታዙን ከዳዕዋው ለማስቆምና ማይኩን እዘጋለሁ ብሎ ሲታገል ይታያል።

ይህ'ኔ እዛው ባንክ ውስጥ የርሱ ቢሮ ላይ የማሪያምና የእየሱስ ስዕል የሚሉትን ለጥፎ ሊገኝ ይችላል፤ ወይንም የሆነ ከበዓላቸው ጋር የተያያዘ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ወይም የሆነ የነርሱው ኃይማኖታዊ ጥቅስ ሊገኝ ይችላል።

በጣም የሚገርመኝ ነገር ሌላውን ይተውና የሙስሊሙ ጊዜ ጥላቻቸውን በሴኪዩላሪዝም ሽፋን ህግ ለመተግበር ሲፍጨረጨሩ ይታያሉ።

ባንኩ የእምነት መስበኪያ አይደለም ብሎ የማይገናኘውን ለማገናኘት ሞከረ እንጂ ይህ'ኔ ባንኩ ራሱ ለቤተ ክርስቲያን አስራት ይከፍል ይሆናል፤ ወይንም የሆነ ውስጣዊ መዋጮና ድጋፍ ላይ ይሳተፍ ይሆናል።

በአንዳንድ ሙስሊም ጠል ሠራተኞቹ ሳቢያ ይባስ ብዙ ሚስጥር ታስወጡንና ባንኩንም ቢዝነሱንም ትጎዱታላችሁ።

ከባንኩ በብዛት ርቀት ላይ እየተካሄደ የነበረን ዳዕዋ ይረብሻል ብሎ ለማስቆም መሞከር ዘዴ ፍለጋ ነው።

በነበረው ነገር አፍረናል። አቢሲኒያ ባንክ በተለይም የዚያ ቅርንጫፍ ኃላፊ ኡስታዝ ሙሐመድ ኸዽርንና ታዳሚውን ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል።

ኡስታዝ ሙሐመድ ኸዽር ደግሞ ሐቅም ስለነበረው ማይኩን አትዘጋም ብሎ ያስቆመበት መንገድም ተገቢ ነው ባይ ነኝ።

በንፅፅር ላይ የተሰማራችሁ ወንድሞች በጥቅሉ በርቱ፤ ከመልካም ጸባይ ጋር የእስልምናን ውበት አሳዩ።

||

t.me/MuradTadesse

9 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group