Translation is not possible.

«ሒጃባችሁን ካላወለቃችሁ ፈተና ላይ አትቀመጡም‼»

በዩኒቨርሲቲ ደረጃ የዚህ አይነት የወረደ አመለካከት የሚያራምዱ ጽንፈኛ መምህራን መኖራቸው ግልፅ ነው ግን እዚሁ በዋና ከተማችን አዲስ አበባ ውስጥ እህቶቸችን «ሒጃባችሁን ካላወለቃችሁ ፈተና ላይ አትቀመጡም‼» እየተባሉ ከሆነ ተማሪዎቹ ሳይሆኑ የሀገሪቱ ሙስሊም ማህበረሰብ ምላሽ የመስጠት ኃላፊነት አለበት ተጣርቶ እርምጃ መወሰድም አለበት።

አንዳንድ ታዋቂ ሰዎች ኒቃብ አስገዳጅ አይደለም እያሉ የተናገሩት የደካሞች ንግግር ጠንካራ እህቶችን ተጋላጭ እያደረገ ይገኛል ምክንያቱም አሁን ላይ ሂጃብ ራሱ መልበስ አትችሉም ወደማለት መጡ ስለዚህ ጠንካራ ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል፡፡

«አትፈተኑም ብሏል የተባለው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብት ትምህርት መምህር ነው። 2ኛ አመት ተማሪዎችን final exam ለመፈተን በገባበበት ሰአት ሒጃቢስቶችን ወይ ሂጃባችሁን አውልቁ ወይ ደግሞ ክላሱን ለቃችሁ ውጡ በማለት በእብሪት ተናግሯል። የአንዲት እህትንም ሒጃብ ለማውለቅ ሙከራ አድርጓል። ልትወጣ ስትል ተመለሺ ብሎ ተመልሳ ብትፈተንም እሷ ላይና ሌሎች ሒጃቢስቶች ላይ በሙሉ ፈርሟል ተብሏል።

አንድ መምህር የአንዲት ሴትን ልብስ ለማውጣት መሞከር ራሱ እጅግ አስነዋሪ ድርጊት ነው በተማሪዎቹ ላይም ትልቅ የስነ ልቦና ጫና ይፈጥራል ምናልባት በጣም ጎበዝ ካልሆኑ ፈተናውን ራሱ ተረጋግተው አልሰሩም ማለት ነው፡፡

ይህ ድፍረት እና ሙስሊም ጠልነት በጊዜ ሊታረም ይገባል ሂጃቧን ለማውለቅ የሞከረባትን ተማሪንም ይቅርታ መጠየቅ አለበት ዩኒቨርሲቲውም 20ኛው ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ ላይ የተቸነከሩ መምህራን ጋር ከመንቀራፈፍ ወጥቶ ተራማጅ መሆን አለበት፡፡

የጊቢው ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ጉዳዩን አጠንክሮ መያዝ አለበት!

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group