Translation is not possible.

ቱርክ ለእስራኤል ሲሰልሉ ነበር ያለቻቸውን 7 ሰዎችን በቁጥጥር ስር አዋለች!

የቱርክ ፖሊስ ለእስራኤል የስለላ አገልግሎት ሞሳድ መረጃ በመስጠት የተጠረጠሩ ሰባት ሰዎችን በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን ግለሰቦቹ መረጃዎችን በግል መርማሪዎች በኩል ለስለላ ቢሮዎች አስተላልፈዋል መባሉን መንግስታዊው አናዶሉ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከቱርክ ብሄራዊ መረጃ ድርጅት ወይም (MIT) ጋር በመተባበር በኢስታንቡል እና በኢዝሚር ከተማ ባካሄደው ዘመቻ ነው፡፡ ሞሳድ በቱርክ ውስጥ በሚኖሩ የውጭ ዜጎች ላይ ለሚያካሂደው ስለላ በቱርክ ውስጥ የሚኖሩ ፍልስጤማውያንን እና የሶሪያ ዜጎችን መመልመሉ ተሰምቷል።

ባለፈው ወር 34 ሰዎች በጋዛ ውስጥ ስላለው ጦርነት ለእስራኤል በመሰለል ተጠርጥረው በቱርክ ፖሊስ ተይዘው ታስረዋል።

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group