Tidak bisa diterjemahkan.

ጉድህን ተመልከት‼

===============

(ገንዘብህ የት የት እንዳለ ና ላሳይህ!)

||

✍ ስለ ባንኮች ብዙ ያላስተዋልናቸው ሚስጥሮች አሉ። ባለፈ በፈረንጆቹ ጁን 2023 ላይ በወጣው መረጃ መሠረት በጣም በርካታ ቢሊዮን ብር ከሙስሊሙ የሰበሰቡ ባንኮች አብዛሃኛውን ገንዘብ መልሰው ፋይናንስ አላደረጉም (ለሙስሊሙ አላበደሩም)። በዚህ ረገድ ጀማሪ እንደመሆናቸው መጠን ዘምዘምና ሂጅራ የተሻለ ፋይናንስ አድርገዋል። ሌሎች አንዳንድ ያልጠበቅኳቸው ባንኮችም በአንፃሩ ጥሩ ፋይናንስ አድርገዋል። የኛዎቹ አቅማቸውን ሼር በመግዛት፣ አካውንት በመክፈትና መሰል እገዛዎች ብናጠባክራቸው ኖሮ የሰጠናቸውን መልሶ ለማበደር እንደማይሰስቱ ይህ ያሳያል።

ዋናዎቹ ግን የሙስሊሙን ብር አፍነው ይዘው ምን እየሠሩበት እንደሆነ አላህ ይወቅ። ምናልባትም በወለድ ለሌላ እያበደሩት ይሆናል።

ይሄው ያበደሩት ራሱ ለነማን እንደሆነ አላህ ይወቅ። አይደለም ሌሎቹ የኛዎቹ ራሱ ይሄንን ብድር ለማን፣ በምን መስፍርት፣ ምን አይነት በተጠናና አዋጭ መስክ ላይ፣ እንደት… እንዳበደሩት ለጊዜው እንለፈውና፤ ባንኮች ካጠራቀሙት ላይ እስከ 80% ድረስ መልሰው ፋይናንስ ማድረግ ሲገባቸው ብዙ ብር የሰበሰቡት ባንኮች ግን 10%, 23%, 24% ብቻ ነው ያበደሩት።

የሚሻለን ምን መሰላችሁ፦ ሁሉንም ከወለድ ነፃ – IFB የሚሠሩ ባንኮች፤ ወይ ራሳቸውን ችለው ባንክ ማስደረግና ሙስሊሙ እነዛ ላይ ጭምር ሼር እየገዛ እንዲሳተፍ ማድረግ፣ ወይንም አንድ ወጥ ተቆጣጣሪ ኮሚቴ ተዋቅሮ የሁሉንም ከወለድ ነፃነት መከታተል፣ ለማንና እንደት እንደሚሠሩና እንደሚያበድሩ መቆጣጠር፣ የኛዎቹ ባንኮች በውስጣቸው ያለውን አንዳንድ የብድር አሰጣጥ፣ የሠራተኛ ቅጥር፣ የውጭ ምንዛሬ አሰጣጥ፣ በአካባቢያዊነትና ትውውቅ የቆሸሸ አካሄድ አጸዳድቶ አቅማቸውን ማጠንከር፣ ሼር መግዛት፣ አካውንት መክፈት፣ አሠራራቸውን ማዘመን፣ ሙያን ለባለሙያ ሰጥቶ እድገታቸውን ማፋጠን፤ ለነገ ይደር የማይባል የሁላችንም የቤት ሥራ ነው። ባይሆን ከውጭ ውበት ይልቅ የውስጥ ጽዳት ይቀድማልና ከዚያ በመጀመር፤ ማንም ቅሬታ የሌለበት አካታችና ሁሉም የራሴ ብሎ የሚያያቸው፣ ለነገ ከፍታቸው ሲባል ዛሬ በሙያውም፣ በገንዘቡም መስዋዕትነት የሚከፍልላቸው ባንኮች እናደርጋቸዋለን ኢንሻ አላህ።

||

t.me/MuradTadesse

fb.com/MuraadTadesse

image
Kirim sebagai pesan
Bagikan di halaman saya
Bagikan di grup