Translation is not possible.

በተለምዶ አግራው ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን የቢላል መስጂድን ይዞታ ዛሬ በማጠር አስከብረናል።ጊዚያዊ መስጂድም እየተገነባ ይገኛል።በቀጣይ በዚያው ክፍለ ከተማ የይገባኛል ጥያቄ የተነሳበትን ሌላ ቦታ ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር ችግሩን ፈተን በቅርቡ ይዞታውን የምናስከብር ይሆናል።ኢንሻአ አሏህ።

በኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት በተለምዶ አግራው በሚል ስያሜ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው ቢላል መስጂድ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ህጋዊ ጋርታና የአጥር ፍቃድ ይዞ ቦታውን ለማስከበር ሲንቀሳቀስ አንድ ግለሰብ በሀሰት ህገ-ወጥ ግንባታ እየተካሄደ በመሆኑ ሁከትና ብጥብጥ ሊነሳ ነው በማለት የአጥር ግንባታዊ ሂደት እንዲስተጓጎል አድርጎ እንደነበር ይታወቃል።

ሆኖም የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤትና በተዋረድ ያለው መዋቅር በተለይም የክፍለ ከተማው የእስልምና ጉዳዮች አመራሮች፣የመስጂዱ ኮሚቴና የከፍተኛ ም/ቤታችን ጉዳይ አስፈፃሚዎች በአካባቢው ሙስሊም ማኀበረሰብ ድጋፍ ሰጪነት በመታገዝ እና የክፍለ ከተማው እና የወረዳው የመሬት ማኔጅመንትና የሰላምና ፀጥታ አመራሮች በጋራ በመሆን ባደረጉት ርብርብ መስጂዱ በዛሬው እለት ይዞታው እንዲታጠር ተደርጓል በአሁን ሰዐት የአካባቢው ሙስሊም በመረባረብ ጊዚያዊ መስጂዱንም በመገንባት ላይ ይገኛል።

በሌላ በኩል በዚያው በኮልፌ ክፍለ ከተማ ለመስጂድ መገንቢያ ቦታ በህጋዊ ካርታ ተሰጥቶን የአጥር ፍቃድ ካወጣን በኃላ ይገባኛ የሚል አካል በመፈጠሩ ምክንያት ቦታው ሳይከበር የቀረ ቢሆን ከሚመለከተው አካል ጋር እየተነጋገር ጉዳዩን ለመፍታት ዳር ደርሰናል።በቅርቡም ቦታውን የምናስከበር ይሆናል ኢንሻ አላህ።

6 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group