Translation is not possible.

ሸይኽ ኢልያስ አሕመድን ትናንት በኢሙ ታወር በነበረው ስብሰባ ላይ በተዋቀረው የአዲስ አበባ መጅሊስ የፈታዋ ኮሚቴ አባላት ውስጥ ተካቶ ስላየሁት ደስ ብሎኛል።

ሸይኹ ፈቃደኝነቱ ተጠይቆ ከአዲስ አበባ መጅሊስም አልፎ ወደ ፌዴራል መጅሊስም ጭምር ልክ እንደ ፈታዋ ኮሚቴ ባሉ ዒልም በሚጠይቁ ቦታዎች ላይ ቢቀመጥ ሚሊዮኖችን የሚጠቅም አቅም እንዳለው አምናለሁ።

አላህ ባለበት ሁሉ ይጠብቀው።

መጅሊስም ዕውቀት በሚሹ ቦታዎች ላይ ትክክለኛ የዕውቀት ባለቤቶችን ወደፊት ካመጣ በአላህ ፈቃድ ተጨባጭ ለውጥ እናያለን ብዬ አስባለሁ።

ባይሆን የአዲስ አበባ መጅሊስ ከህዝ ሙስሊሙም ሆነ ከክፍለ ከተማ መጅሊሶች ዕውቅና ውጭ ያለ ምንም ህጋዊ አግባብ የአንድን አሶሴሽንና አጋሮቹን ጥማት ለማርካት ብሎ በጓሮ ደብቆ የመረጣቸውን 8 የምክር ቤት አባላት ከነ ውስጠ ሚስጥሩ የተረሳለት እንዳይመስለው። ከህዝብ የሚደበቅ ሚስጥር የለም። ነገሩ የአንድ ሰሞን ጩኸት ብቻ መስሎት እንዳይሸወድ። ችግር ባየን ቁጥር ሁሉ ይህን እኩይ ሥራውን እንዘክርለታለን። ጉዳዩ በአደባባይ በስፋት ተወርቶ የልዩነት አጀንዳ ከሚሆን ይልቅ፤ በውስጥ እንዳበላሸው ሁሉ በውስጥ ቢያስተካክለው ይመረጣል።

በተረፈ ግን በርቱ!

||

t.me/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group