Translation is not possible.

ስለ ባንኮች ይህን መረጃ ታውቁ ኖሯል⁉️

===========================

(ሁሉም ሙስሊም ይህን ዳታ ማወቅ አለበት፤ አሰራጩት!)

||

✍ በሃገራችን ውስጥ ኢስላማዊ ባንኮችን ጨምሮ በአሁኑ ወቅት 31 ገደማ ባንኮች ይገኛሉ።

በሁሉም ባንክ አጠቃላይ የሚገኝ ገንዘብ 2.2+ ትሪሊዮን ብር ነው ተብሎ ይገመታል።

ከዚህ መካከል 2 ትሪሊዮን ብር የሚሆነው በወለድ የተቀመጠ ሲሆን 0.2 ትሪሊዮን (200 ቢሊዮን) ብር የሚሆነው ከወለድ ነፃ በሚባሉት ውስጥ የሚገኝ ነው።

ከዚህ ከ200 ቢሊዮኑ ውስጥ ግማሹ (100 ቢሊዮኑ ብር) በንግድ ባንክ ብቻ ሲሆን፤ ቀሪው መቶ ቢሊዮን በአዋሽ ኢኽላስ፣ በኢሲኒያ አሚን፣ በዳሽን፣… በአጠቃላይ የወለድ ባንኮች ከወለድ ነፃ ብለው በከፈቱት መስኮት እንዲሁም በዘምዘምና ሂጅራ ውስጥ ይገኛል። የዘምዘምና የሂጅራው 10 ቢሊዮን ገደማ ብቻ ቢሆን ነው።

√ ያኔ ከ10+ አመታት በፊት ኢስላማዊ ባንክ ይቋቋም ተብሎ ሙስሊሙ ሲጠይቅ ዘምዘም ባንክ ሊጀመር ሲል መታገዱ ይታወሳል።

በምትኩ ከ"ወለድ ነፃ (Interest Free Bank - IFB" አሉና በወለዱ መስኮት በሽንገላ በፈረንጆቹ 2013 ላይ ተጀመረ።

በአመቱ (2014) ላይ በዚህ ከወለድ ነፃ መስኮት ተቀማጭ የነበረው አጠቃላይ ገንዘብ 600 ሚሊዮን ብር ነበር። የግል ባንኮችም ይህን መስኮት መክፈት ሲጀምሩ 3 ቢሊዮን፣ ከዚያም ወደ 12 ቢሊዮን ብር አደገ።

ከ4 አመታት በፊት (2020 ላይ) አጠቃላይ ከወለድ ነፃ ተብሎ የተጠራቀመው ገንዘብ 57 ቢሊዮን ብር ብቻ ነበር። ከዚያ ውስጥ በብድር መልክ የተሰጠው (ፋይናንስ የተደረገው) 13 ቢሊዮኑ ብቻ ነበር። ግን እስከ 85% ፋይናንስ መደረግ ነበረበት።

2021 ላይ ዘምዘምና ሂጅራህ ሲጀምሩ፤ ሁሉም በማስታወቂያውም በምኑም እየታገለ ወደ 100 ቢሊዮን አደገ።

አሁን 2023 ላይ 200 ቢሊዮን ደርሷል። ከዚያ ውስጥ 78 ቢሊዮኑ ፋይናንስ ተደርጓል። ዘምዘምና ሂጅራ እንደ አማራጭ ባይመጡ ኖሮ እንኳን 78፤ 28ቱም አይደረግም ነበር።

ዘምዘምና ሂጅራ አቅም ኖሯቸው ባያበድሩን እንኳ፤ እነርሱ አማራጭ ስላሏቸው ወደነርሱ እንዳይሸሹብን ተብሎ ተፈርቶ ሌላው እንዲያበድረን ደህና ማስፈራሪያ በመሆን ጠቅመውናል።

ዘንድሮ ሁሉም ባንኮች ከ70 ቢሊዮን ብር በላይ አትርፈዋል። ግን ሼር ሆልደራቸው ሙስሊም ስላልሆነ ሙስሊሙ የሚከፋፈለው ትርፍ የለም።

ከወለድ ነፃ ብለው በከፈቱት መስኮት የነርሱ ማትረፊያና ኪስ ማድለቢያ ሆንን እንጂ!

√ ሁሉም ባንኮች 1.4 ትሪሊዮን ብር አበድረዋል። ግን 1.34 ትሪሊዮኑ በወለድ ነው። ከወለድ ነፃው 78 ቢሊዮን ብቻ ነው። ነገር ግን ማጠራቀሙ ላይ ስናይ ካለው 2 ትሪሊዮን ገንዘብ 1+ ትሪሊዮኑ የሙስሊም ነው ተብሎ ይገመታል።

√ የሃገራችንን ህዝብ ብዛት አስቡት። አጠቃላይ በሁሉም ባንኮች 129 ሚሊዮን የባንክ አካውንቶች ተከፍተዋል። የዘምዘም፣ የሂጅራ፣ የራሚስና የሸበሌ አካውንት ግን ተደምሮ እንኳ 1 ሚሊዮን አይሞላም። ለምሳሌ፦ የዘምዘም 360,000 ብቻ ነው። ሲራ ሲጀምር ከነበሩት 12,750 ሼር ሆልደሮቹ መካከል ግማሹ (6,118) የሚሆኑት አካውንት አልከፈቱም። አስቡት! ሼር ሆልደር ሆኖ እንኳ አካውንት ያልከፈተ አለ። ቆይ ምናችንን ነው ግን የሚያመን?

ከ129 ሚሊዮኑ አካውንት ውስጥ በኢስላማዊ ባንኮች የተከፈተው አካውንት 1 ሚሊዮን ያልሞላው 129 ሚሊዮኑ ሁሉ የሌላ እምነት ተከታይ ሆኖ እንዳይመስላችሁ። ከ60+ ሚሊዮን ሙስሊም ውስጥ 16% ገደማ ብቻ ነው አካውንት የከፈተው።

√ ከዘምዘምና ሂጅራ መመስረት በኋላ የመጣው አማራ ባንክ ገና ሲጀምር የከፈታቸው 75/80+ ቅርንጫፎች ዘምዘምና ሂጅራ አሁን ድረስ የሏቸውም። አሁን እርሱ 300 ገደማ ቅርንጫፍ ደርሷል። ዘምዘም ሥራ ሲጀምር የተከፈለ ካፒታሉ 871 ሚሊዮን ብር ነበር። የተመዘገበ ካፒታሉ ደግሞ 1.6 ቢሊዮን። አማራ ባንክ ግን የተከፈለ ካፒታሉ ብቻ 8 ቢሊዮን ነበር። የተመዘገበው ደግሞ 10 ቢሊዮን።

አሁን በሁሉም የሃገሪቱ ክልሎች ውስጥ የሚገኘው ሙስሊም ብዛቱ ከአንድ ክልል ህዝብ አንሶ ነው? ወይንስ ምን ነክቶን ነው?

እንደዛ በትግል እንዳልተገኙ፤ አሁን ላይ ለምንድን ነው ሳንጠቀምባቸው የቀረነው?

የኛ ገንዘብ ከወለድ ነፃ ሌሎች ጋር ስለምናስቀምጥ፤ ወይ ለኛው አያበድሩን፣ ወይ ዘካ አያወጡ፤… የኛ ገንዘብ የሚያስገኘውንም ወለድ፣ ዋናውንም አድርገው ለራሳቸው ሰው ያበድሩታል።

የኛ ባንኮች እዚህ 5 ቢሊዮን እንኳ መሙላት ተስኗቸው ያጣጥራሉ።

ኧረ! እስኪ ይቆጨን። መረጃዎችንና ዳታዎችን፣ መፍትሄዎችንና ያሉ ችግሮችን እንወያይባቸው። በደንብ ይፋፋም ይህ ሃሳብ!

በአላህ ፈቃድ የሆነ ነገር ላይ እንድረስ‼

Send as a message
Share on my page
Share in the group