Translation is not possible.
🍃"13ቱ" የጥሩ ሚስት መገለጫዎች🍃
 
① የትም ብትሆን አላህን ትፈራለች፣ በሁሉም ነገር የነቢዩን  ሱና ትከተላለች
 
②ባሏ ያዘዛትን በሙሉ -ከዲን ጋር የሚጋጭ እስካልሆነ ድረስ- ትታዘዛለች
 
③ከሷ ጥሩን ነገር እንጂ እንዳያይ፣ እንዳይሰማና እንዳያሸት ጥረት ታደርጋለች
④ቤትና ንብረቱን እንዲሁም
    ቤተ-ሰቦቹን ትጠብቃለች
 
⑤እሱ የማይፈልገውን ሰው
     አትጠጋም አታስጠጋምም
⑥ ባሏን ሳታሳውቅ ሱና ጾም አትጾምም 
      ከቤትም አትወጣም
 
⑦ የባሏንና የቤቷን ሚስጥር
      በሚገባ ትጠብቃለች
 
⑧ ባሏን በመልካም ነገር ላይ
ታግዛለች ሲሰንፍ ታበረታታዋለች፣
   ሲረሳ ታስታውሳለች
 
⑨ሐላል ከስብ እንዲከስብ ሐራምን እንዲርቅ ዘወትር ትገፋፋዋለች፣ለእሷና ለቤቱ ብሎ ዲኑ የማይፈቅደውን ስራ   እንዳይሰራም ታሳስበዋለች
 
①∅ ደስታና ሃዘኑን ትጋራለች፥
እርሱ ሐሳብና ጭንቀት ውስጥ ሆኖም እሷ አትስቅም፣ እሱ ማረፍና መደሰት በሚፈልግበት ወቅት ላይም እሷ በተቃራኒው ተከፍታ አታስከፋውም
 
①①በሚያደርግላት ነገር በሙሉ 
   ይብዛም ይነስ ታመሰግነዋለች
 
①② ቤቷን እያቀዘቀች የሰው ቤት አታሞቅም ቤቷንም እያፈረሰች
    የሰው ቤት አትገነባም!
 
①③ አላህ የሰጣትን ልጆች በኢስላም ስርዓት ቀርጻ ታሳድጋለች ትልቁ የእሷ ስራም ይህ እንደሆነ በማወቅ በስራዋ ትኮራለች! ልጅም ያጣች እንደሆነ ታግሳ ተስፋ ሳትቆርጥ ጌታዋን ትለምናለች
          አበቃ
Send as a message
Share on my page
Share in the group