Çeviri imkansız.

ኢብራሂም አል_ነኸዒ (አቡ ዒምራን) ማየት የተሳነው ሰው ነበር። ተማሪው የሆነው ሱለይማን ቢን ሚህራን (አዕመሽ) ደግሞ ዓይኑ ሸውራራ (ድክመት ያለበት) ነበር። የሁለቱ ታሪክ ኢብኑ ጀውዝይ እንዲህ ዘግቦታል……

ከእለታት አንድ ቀን ሁለቱም "ኩፋ" ወደ ተባለ ሀገር ጉዞ ይጀምራሉ። በመንገዳቸው በመሄድ ላይ ሳሉ ኢማሙ ነኸዒ እንዲህ ይላል

"ሱለይማን ሆይ! አንተ ሌላ መንገድ ይዘህ፤ እኔም ሌላ መንገድ ይዤ ብሄድ ምን ይመስልሃል?

ምክንያቱም; እነዚህ ሰዎች ካዩን “እውር በሸውራራ እየተመራ ነው” ብለው አሹፈውብን (አምተውን) ወንጀል ላይ እንዳይወድቁ እፈራለሁ" አለው።

አዕመሽ ደግሞ

"አቡ ዒምራን ሆይ! እነርሱ ወንጀል ላይ ወድቀው እኛ ብንመነዳ ምን ትጎዳለህ?"

ሲለው

ኢብራሂም ነኸዒ

"ያ ሱብሃነላህ! እኛ ሰላም ሆነን እነርሱም ሰላም መሆናቸው፤

እነርሱ ተወንጅለው እኛ ከምንመነዳ ይሻላል" አለው።

👆እንዲህ ከክፋትና ከጥላቻ የጠራ በሆነ ቀልብ ነው አባቶቻችን ይህንን ውብ የሆነ እስልምና ያስተላለፉልን።

እኛስ ለሙስሊም ወንድሞቻችን ያለን አስተሳሰብ ምን ይመስላል?!

ሁሉም ራሱን ይፈትሽ❕

ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇

┏━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┓

@tolehaahmed

┗━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┛

Mesaj olarak gönder
Sayfamda paylaş
Grupta paylaş