ምርጥ ባልና ሚስቶች ማለት

ራሳቸውን ለአላህ የሰጡ ናቸው፡፡ ይህ ማለት በትዳር ህይወታቸው የሚያጋጥማቸውን ነገር ለአላህ በመተው በሶብር ያሳልፉታል፡፡

ባል ሚስቱን ቢያስቀይማት ራሷን ለአላህ አሳልፋ የሰጠች ናትና የጌታዋን ሽልማት ለማግኘት ይቅር ትለዋለች ባልም እንደዛው፡፡

በትዳራቸው ውስጥ ሙሲባ ችግር ቢያጋጥማቸው እርስ በርስ መወቃቀስ ሳይሆን አላህ ነው ያመጣው በማለት ሶብር ያደርጋሉ  ይታገሳሉ፡፡ በደስታቸው ጊዜም አላህን ያመሰግናሉ፡፡ በሁሉም እንቅስቃሴያቸው አላህን ከጎናቸው ያደርጋሉ፡፡

መጥፎ ነገር ባየባት ጊዜ አይቧን ገመናዋን ለማንም ከመናገር ይልቅ የርሱን አይብ ገመና ነገ የውመል ቂያማ አላህ እንዲሸፍንለት ይደብቅላታል እርሷም ልክ እንደዛው፡፡

በኢባዳ ላይ እርስ በርሳቸው ይተጋገዛሉ  አንዱ በዘነጋ ጊዜ ሌላኛው ያስታውሳል፡፡ ይህ ነው ምርጥ ባልና ሚስት ማለት አላህ ይወፍቀን።

   

Mesaj olarak gönder
Sayfamda paylaş
Grupta paylaş