Хьо дакъа дацанаш махь йоьтта.

በአማራ ክልል ሙስሊሞች ላይ በየዕለቱ እየተፈጸሙ ያሉ ግፎች ብዙ ናቸው። በተለይም እየታገቱ ሚሊዮን ገንዘቦችን የሚጠየቁና ያንን መክፈል ካልቻሉ የሚገደሉ ብዙዎች ናቸው።

በተደጋጋሚ ከበርካታ የክልሉ አካባቢዎች መረጃዎች በስልክም በውስጥም ይደርሱኛል።

ግን ያው ይህን አድራጊዎቹ አካላት ከመንግስት ጋር እየተዋጉ ስለሆነ ከአላህ ውጭ ለማን ይነገራል ብዬ አልፌዋለሁ፤ አንዳንዴም ሚዲያ ላይ ከወጣ የበለጠ ትኩረት እንዳያደርጓቸው ብዬ ነበር። ግን ትኩረት መደረግ አልቀረላቸውም። አይደለም ሌሊት ቀን ላይ እንኳ መስጅድ ወጥቶ ሰግዶ በሰላም ለመመለስ የተቸገሩበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል።

ቢያንስ በዱዓእ እንኳ አንርሳቸው።

አንድ ወንድም አሁን የላከልኝ መልዕክት እንዲህ ይላል፦

«ebakh murad bahirdar leminoru muslimoch demts hunlen You have no idea mn yakl yekefa huneta west endalu muslimochn becha netlew eyafenu b millionoch birrr eytyeku nw lemsale k tenant wediya mesjid zuhur lisegd yehedewn abat bekenu b bajaj afnew wesedut keza 2.5 million birr teyeku ahun muslim kehonk beken enkuan bechahn menkesaks ematchlbet huneta lay dersual»

አላሁ-ል-ሙስተዓን!

የሚያሳዝነው ነገር ውጭ ሃገር (በተለይም ዐረብ ሃገር) ሆነው አጋቾችን የነፃነት ታጋይ አድርገው ብር በመላክ የሚደግፉ በርካታ እህትና ወንድሞች መኖራቸው ነው። ለፍተው ባገኙት ገንዘብ ድጋፍ ቤተሰቦቻቸውንና ወገኖቻቸውን አጋች የሆነን ኃይል ማሳገት መርዳት ያሳዝናል።

© murad tadsse

Send as a message
Share on my page
Share in the group