Translation is not possible.

አሳዛኝ ታሪክ  ። እናቴን ማን ነው የሚገዛኝ ?

💞ኡሚ ኡሚ ኡሚ 💞

አንድ ወጣት በጣም ቆንጆ የሆነች ልጅ ይወድና  ለጋብቻ ያጫታል ከተጫጩ  በኃላ ግን ግልፅ  በሆነ አረፍተ ነገር እናቱን እንደማትወዳት እና  አብራቸው መኖር እንደማትፈልግ ትነግረዋለች ።

እሱን  ብትወደውም እናቱን ግን ልትወድለት አልቻለችም እናቱም

በእድሜ የገፉ ስለነበሩ ልጂቷ  ብዙ ታስቸግራቸው ጀመር።

ከዛም ልጅ እንደማያገባትና እንደሚለቃት አስረግጦ ሲነግራት ልጂቱ ልጁን  ስለምትወደው ደነገጠች እንደምታስተካክልና እናቱን እንደምታከብር እንዲያገባት ተማፀነችው።

ልጁም ካስተካከልሽ ብሎ እሽ አላት ከዛም የሰርጋቸው ቀን ደረሰ ምሽቱ ላይ ሠዎች በተሰበሰቡበት መሐል እናቱ ተጋባዥ እንግዶችን  ለማስተናገድ በደስታ ሽር ጉድ ሲሉ

ሙሽሪት በንዴት ይህችን አሮጊት እናትክን ወዲያ በልልኝ አታሳየኝ ከቻልክ እንደውም ሽጣት አለችው።

ልጁም ፈገግ ብሎ ተነሳና ሰዎች ከተሰበሰቡት መካከል

እናቴን ማን ነው የሚገዛኝ "ለ 3 ጊዜ በተከታታይ ማለት ጀመረ

እናቱም ከልጃቸው አንደበት የሰሙትን ማመን  አቃታቸው ማዘንና ማልቀስ ጀመሩ እንግዶቹን በጣም  ተገረሙ አዘኑ ከዛም ሙሽራው ወደ ሙሽሪት ዘወር አለና

"አየሽ እናቴን ማንም ሊገዛት አልቻለም

ለምን  እንደሆነ ታቂያለሽ? ምክንያቱም እናት ውድ ነች እናቴ ከምንም በላይ ውድ ነች ዋጋ አይተምናትም እኔ ግን

እናቴን እገዛታለው አንችን ደግሞ ሸጨሻለው

ፈትቼሻለው በማለት የሰርጉ ቀን ቀለበቱን  ከፊቷ ላይ በመወርወር ትቶላት እናቱን ይዞ ሲወጣ ወዲያው ከእንግዶቹ አንዱ ተከተለውና እንዲህ  አለው "

ለሴት ልጄ ከአንተ የተሻለ ጥሩ ልጅ

አላገኝም ፍቃደኛ ከሆንክ ልጄን ልዳርልክ

ብሎት ልጁን ይዞ ወደ ቤቱ ወሰደው ልጁም የዛን ሰው ልጅ ሲመለከታት እጅግ ውብና አደበኛ ነበረች አገባትም ለባሏም ሆነ ለባሏ እናት ፍቅሯን ያለ ገደብ ትሰጣቸውና ትንከባከባቸው ጀመር።

የወለደቻት እናቷ እስክትመስላት ድረስ

የሚጠበቅባትን ሁሉ መወጣት ጀመረች።

መልካምና  ደስተኛ የሆነ ህይወት ይኖሩ ጀመር።

አንድን ነገር ለ አሏህ ብሎ የተወ አሏህ የተሻለውን ይወፍቀዋል

እህቴ ከታሪኩ ብዙ ቁምነገሮችን ተማሪበት፣ ለጓደኞችሽም አጋሪው።

"ወደ መልካም ነገር  ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

Send as a message
Share on my page
Share in the group