Translation is not possible.

አራት ትልልቅ ጥቅሞቺ በጁምአ

➊ ለጁመአ ሰላት መዘጋጀትና መማለድ ያለው ጥቅም

ረሱል (ﷺ) እንዲህ አሉ፡-

ለጁምአ ሶላት ያስታጠበና የታጠበ ከዚያም የማለደና በመጓጓዣ ሳይሆን በእግሩ የሄደ ፡ ከኢማሙ ቀርቦ ሳያለግጥ ያዳመጠ ሰው፡

በየ እርምጃው ሌሊቱን ቁሞ ቀኑን ፁሞ እንዳሳለፈው አንድ አመት ኢባዳ ያገኛል ፡፡

የጁምዐ እለት ታጥቦና በሚቺለው ፀድቶ ቅባቱን ተቀብቶ ወይም ከቤተሰቡ ሽቶ እንኳን ቢሆን ተቀብቶ ወደ መስጅድ የሄደ፡ በሁለት ሰዎቺ መካከል ሳይለያይ አላህ ያለለትን ሰግዶና ኢማሙ ሲናገር ፀጥ ብሎ አዳምጦ የተመለሰ ሰው እስከሚቀጥለው ጁምአ ድረስ ያለው ወንጀል ይማርለታል ፡፡

➋ ረሱል (ﷺ) ሰላዋት ማውረድ ጥቅም

ነብዩ ﷺ እንዲህ አሉ ፡-

አንድ ግዜ በእኔ ላይ ሶለዋት ያወረደ ሰው በእርሱ ላይ አላህ አስር ጊዜ ሶለዋት ያወርድበታል ፡ አስር መንጀልም ይሰረዝለታል፡ አስር ደረጃ ይጨመርለታል ፡፡

➌ የሱረቱ ከህፍ (ከዋሻ ምዕራፍ ) መቅራት ጥቅም

ነብዩ ﷺ እንዲህ አሉ ፡-

ከሱረቱ ከህፍ አስር አንቀፅ የሐፈዘ ሰው ከደጃል ተንኮል ይጠበቃል፡ ደጃልን ያገኝ ሰው በሱ ላይ ሱረቱል ከህፍ መግቢያ ያንብበት ብለዋል ፡፡

የጁምዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀራ ሰው አላህ በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል ብርሃን ያበራለታል ፡፡

➍ በጁምዐ ቀን ዱአ ማረግ ጥቅም

አላህ በጁመአ ቀን የዱአ አድራጊን ዱአ የማይመልስበት (ዱአውን የሚቀበልበት ) አንድ ሰአት አለቺ ብለዋል ፡፡

ዑለሞቺ በተለይም የቀኑ መጨረሻ ሰአት ላይ እንደሆነ ተናግረዋል ፡፡

አላህ የምንጠቀምበት ያድርገን !!!

Send as a message
Share on my page
Share in the group