Табасаранан алхьа кха дац.

☞ኒቃብ☜  

➺ያንችነት ምንነት ውበት መገለጫሽ

ሀሉን መጠበቂያ ግርማ ያንችነትሽ

የሱና ነፀብራቅ ውበት ማንነትሽ!

➺እንቁ ሽልምልሟ የኔቃቧ ኩሩ

ጠላቴ ቢንገበገቡ ቢቆጩም ቢያወሩ

ድጋይን ፈንቅለው ጉድጓድ ቢቆፍሩ

ድንኳን ለባሽ ብለው ቢጮሁ ቢያወሩ

   ☞ብለሽ ንገሪያቸው!

➺ሰሚ ነኝ ታዛዢ ነኝ ጌታዬን አፍቃሪ

ነብዬን ተከታይ በሱናቸው ሰሪ

ይህ ነው መሰረቴ የሞኖሬ አለማ

አሏህን ብቻ ማምለክ በዱንያው አውድማ

ነገ እንድመነዳ የአሂራውን ምንዳ

ታዛዢ እሆናለሁ ምንም ሳልጓዳ

☞ ብለሽ ንገሪያቸው!

    ቃ

      ቤ

➺መማርን አያቅብ መስሬቴን አይገታ

ሀራም ከሌለበት ድብልቅ ጋጋታ

አይተው ከመፍተን የተጠበኩበት

ገና በሩቅ ሲያዩኝ የምከበርበት

ታዝዢ መልበሴ ኔቃቤን ወደድኩት

መልካም አማላካች ትውልድን ቀያሪ

የሱና ተከታይ ድኔንም አክባሪ

አወ አመልካች ነኝ እኔ መልካም አስተዋፆ

ትውልዶችን መልማይ በኢስላም አንፆ

ይህን የቸረኝ አሏህ ምስጋና ይገባው

እኔስ ተደነቅኩኝ ለታላቅ ልእልናው!

✍አቡ ዑበይዳህ ሶላሁድን

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/joinchat/T9K6KptHSDQ2ZTI0

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group