Translation is not possible.

ጌታችን ሆይ! በእዝነትህ ከመልካሙ...‼️

▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬

✍ምንም ስራ ምን በእያንዳንዱ ነገር ላይ ክፍያ አለ። የክፍያው ሁኔታ ቢለያይም ሁሉም ጊዜ-ጊዜውን ጠብቆ የሆነ ጊዜ ላይ ደመወዝህ ይከፈልሃል (ይመለስልሃል) ወይም በተቃራኒው አንተ ትከፍላለህ፤ ብቻ እንደ ስራው ሁሉም ይከፈ'ላል፣ ይከፍላልም።

ይህ የምድርና የዛኛው አለም ተፈፃሚ ህግ ነው።

(እያወራሁ ያለሁት በየወሩ ስለምታገኘው፣ ስለወርሃዊ ደመዝህ አይደለም!)

*

እያወራሁ ያለሁት ሚዛን ላይ ስለሚቀመጡት ስራዎችህ ነው‼️

አዎ! የሚዛኑ ምልሰት በሁለቱም ሃገር አለ።

መዛኙና አከፋፋዩ ሁሉንም ተመልካችና አዋቂ ስለሆነ ሚዛኑ እጅግ ፍትሐዊ ነው። የቅርቡ ቀላል፣ የሩቁ ደግሞ የከፋ ነው። የሩቁን ላስታውስህ እርሱ ጋር ዝምድና፣ አባት፣ እናት፣ ጓደኝነት፣ ወንድምነት፣ እህትነት አይሰራም፤ በመካከል እዝነት የለም።

('ዛሬ ላይ ምንም ብወድህ በዚያ ቀን እይታችን አላውቅህም፣ አታውቀኝም' አይነት ነው አሳውቄሃለሁ!)

-

በሁለቱም ዓለም ከሰራሃውና ከትክክለኛው ደመወዝህ ውጭ ቲ'ፕ የሚባል ነገር የለም። ከሆነም በእዝነቱ ወይ ደግሞ የምድሯ ክፍያህን ወደ ዘላለማዊዋ ዓለምህ አሸጋግሮ አይቶ ባላየ ያልፍህ ይሆናል።

°

መልካምም ስራ፣ መጥፎ የሰራሃው ስራ ሰከንድ፣ ደቂቃ፣ ሰዓት፣ ቀን፣ ሳምንት፣ ወርና አመቷ ሳትረሳና ሳትዘለል ደመወዝህ አመፅም ሆነ ፅድቅ በ2ቱ ስራህ ተባዝቶና × ተቃንሶ - ሒሳቡ ተሰርቶ በ2ቱም ዓለም አንተው ጋር ይመጣል።

.

የዚህ አለም ኮንትራት የጊዜ ገደብህ እስከሚያበቃ ብዙ ምርጫ አለህ... ለትእዛዙ መገዛት ወይ ማመፅ፣ ማባዛት ወይ ማካፈል፣ መስራት ወይ መተኛት፣ መደሰት ወይ መከፋት፣ ሩቁ ወይ ቅርቡ፣ ጀነት ወይ ጀሃነም፣ መከ'ፈል ወይ ደግሞ መክፈል...

የቱ እንደሚሻልህ ምርጫውን ላንተው ልተውልህ‼️

«ለአንተ ከእርሱ ውጭና ከአንተ በላይ አዛኝ የለም። ለሌሎች አዛኝ በመመስል የሌሎችን ሆድ አትብላ፤ አዛኝነት ከራስ ይጀምራል። ለነፍስህና ለራስህ መልካም ውለታ በመዋል ዋጋ ክፈልለት።»

*

አላህ ሆይ! በዱንያም ሆነ በአኼራ ከፋዮች አታድርገን፤ በእዝነትህ ካንተው ከመልካሙ ክፍያህ ከሚከፈሉት ባሮችህ አድርገን።

ኣሚን🤲

✍አቡ ሒባ ( ጥር 3, 2016 E.C )

-----------------------------------------------

||

የቴሌግራም ቻናል፦

http://t.me//AbuHiba

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group