አፍሪካ ከተኛችበት ከነቃች የአለም ችግር ሳትሆን መፍትሄ ነች!
አሁን ባይመስልም ወይንም ሩቅ ብትሆንም አፍሪካ መልካም መሪዎችና አስተዳደር ካገኘች ካሳለፈችው የመከራ ታሪክ ተነስታ ለአለም ጭቁኖች ፍትህን ልታሰፍን ትችላለች
.
ምን ለማለት ነው! ደቡብ አፍሪካ እስራኤል በፍልስጤማዊያን ላይ የምታደርገዉን የጅምላ ፍጅት መቃወም ብቻ ሳይሆን ጉዳዩን ወደ አለማቀፉ ፍርድቤት ወደ ሄግ በመዉሰድ እስራኤልን በጀኖሳይድ መክሰሷ ይታወቃል፡፡
.
ታድያ እኔን ትዝብት ያጫረብኝ ይህ ሳይሆን የደቡብ አፍሪካው የፍትህ ሚንስትር አልጀዚራ ላይ ቀርበው ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት መልስ ነበር፡፡
.
ጋዜጠኛዋ "ስንት እስራኤልን የሚወቅሱ መንግስታት እያሉ እንዴት ደቡብ አፍሪካ እስራኤልን በጄኖሳይድ መውቀስ ብቻ ሳይሆን ፋይል ከፍታ ልትከስ ቻለች?" የሚል ጥያቄ ታቀርባለች
.
መላሹም የደቡብ አፍሪካው የፍትህ ሚንስትር "ታላቁ አባታችን እና መሪያችን ፍልስጤም ነጻ እስካልወጣች ድረስ ድላችን ሙሉ አይደለም ብለዉን ነበርና ነው" ሲሉ ነው የተደመጡት፡፡
.
ኔልሰን ማንዴላ ስለ ደቡብ አፍሪካዊያን ከአፓርታይድ ነጻ መዉጣት ሲናገሩ " ፍልስጤም ነጻ እስካልወጣች ድረስ ድላችን ሙሉ አይደለም" ሲሉ መናገራቸዉና ዘወትርም ከፍልስጤማዊያን ጎን እንደነበሩ ይታወቃል፡፡
.
ልብ በል! ዉሳኔው ምንም ሆነ ምን፣ ቢወሰን እንኳን ተግባራዊነቱ ምንም ሆነ ምን ሽር ጉድ የሚሉት የአረብ ሀገራትም ሆኑ ቱርክ እረ እንደዉም የፍልስጤሙ ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ ራሳቸው ጨክነው እስራኤል ላይ የክስ መዝገብ አልከፈቱም፡፡ ይህንን የ84 ገጽ የክስ መዝገብ የከፈተችውና ታሪክ መጻፍ የጀመረችው ሃይማኖትም ሆነ አረብነትን መሰረት ያላደረገችው አፍሪካዊቷ ደቡብ አፍሪካ ናት!
ሌሎች ክሱን መክፈት ይቅርና ደቡብ አፍሪካን በያዘችው መንገድ ለማገዝ ድምጻቸዉን አላሰሙም፣ ደቡብ አፍሪካን ከጎንሽ ነን ያሏት አንድ ሃገር ከእስያ (ለጊዜው ያላስታወስኳት) እንዲሁም ቤልጅየም ከአዉሮፓ ናቸው፡፡
.
ለዚህም ነው አፍሪካዊያን ከግለሰብ አምልኮ ወጥተው በትክክል የሚሰራ መንግስታዊ ተቋምና አቋም ከገነቡ ብሎም የጋራ እጣ ፈንታ እንዳላቸው በመረዳት ከተባበሩ ፣ በብዙ ፈተናዎች ዉስጥ ስላለፉ ለግፉዋን መከታ በመሆን የአሁጉሯንም የከፋ ስም በማደስ ለአለማችን የመፍትሄ ምንጭ ለመሆን የቀረቡ ሊሆኑ ይችላሉ ለማለት ነው
.
ይሄው ነው! የናንተስ እይታ ምን የሚሉት ነው?!