✧አንድ ሰው ነበር ላም ለመግዛት ገበያ ሊሄድ ተዘገጃጀና ለሚስቱ እንዲህ አላት  "ገበያ ሄጄ ላም ገዝቼ እመጣለሁ " ይህቺ ሚስት ሳሊሃ ሴት ነበረችና "ኢንሻአላህ " በል አለችው.................ባልየው ግን ኢንሻአላህ ለምን እላለሁ ብሩ በእጄ ነው ስለዚህ ገበያ እሄዳለሁ ላሚቷን ገዝቼ እመጣለሁ አለቀ አላት እና ከቤት ወጣ............... ትንሽ መንገድ እንደተጓዘ የሆነ ወንዝ አገኘና የወንዙን ጥልቀት ጎንበስ ብሎ ሊያይ ሲያጎነብስ የያዘው ብር የሸሚዙ የፊትለፊት ኪስ ውስጥ ነበርና ከኪሱ ወጥቶ ውሃው ውስጥ ይገባበታል.................... ብሩን ለማውጣት ሱሪውን እና ሸሚዙን አውልቆ ውሃው ውስጥ ገባ  በወንዙ አጠገብ የሚያልፉ ሰዎች ልብስ አገኘን ብለው አንስተው ውሰዱበት ሰውየው ከወንዙ ሲወጣ ልብሱ የለም በለበሰው ቁምጣ ብቻ ሆኖ እየሮጠ ወደ ቤቱ ይመለስና በሩጋር ደርሶ በር ሲያንኳኳ ሚስት ከውስጥ ሆና ማነው?  ትላለች አቶ ባል ምን ቢል ጥሩ ነው "እኔ ነኝ ክፈቺ ኢንሻአላህ"

እና ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው በእያንዳንዱ የህይወት እንቅስቃሴያችን ውስጥ " በአላህ ፈቃድ ይሆናል " የሚለውን ሀሳብ መርሳት የለብንም!!  የሆነ ነገርን ለማሳካት ማይክሮ ሰከንዶች ቢቀሩንም እንኳን የዛ ነገር መሳካት እና አለመሳካት በጌታችን እጅ ነው ያለው።..................... ምናልባትም ሞት ሊቀድመን ይችላል #ሞት እጅግ በጣም ቅርብ ነው ስለዚህ እንቅስቃሴያችንን ሁሉ ወደ አላህ እናስጠጋ  ለምናቅዳቸው እቅዶች ሁሉ #ኢንሻአላህ  እንበል

Send as a message
Share on my page
Share in the group