Translation is not possible.

ፖሊስ መረጃውን ይፋ ካደረገው እኛም መልዕክቱን በማሰራጨት እንተባበር።

ሼህ አብዱ ያሲንን በመግደል የሚጠረጠረው መሀመድ ሽኩር አበባው ይፈለጋል። ግለሰቡ እጁን እንዲሰጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል። ተጠርጣረው ያለበትን የሚያውቅ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር አዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል።

*****

አዲስ አበባ ፖሊስ በሼህ አብዱ ሞት የተሠማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው እና ለእምነቱ ተከታዮች መፅናናትን ይመኛል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀሉን ፈፃሚ በቁጥጥር ስር ለማዋል የክትትልና የምርመራ ቡድኖችን አዋቅሮ ክትትሉን አጠናክሮ ቀጥሏል።

የመኖሪያ አድራሻው ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ነዋሪ የነበረ ሟቹ ያሳድጉት የነበረው መሀመድ ሽኩር አበባው ሼህ አብዲ ያሲንን በመግደል ወንጀል ተጠርጥሮ ይፈለጋል።

ስለሆነም መሀመድ ሽኩር አበባው ያለበትን የሚያውቅ ሆነ ማንኛውም መረጃ ያለው በስልክ ቁጥር 011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ ቁጥር 991 መረጃ በመስጠት እንዲተባበር አዲስ አበባ ፖሊስ ያስታውቃል፡፡ በወንጀል የተጠረጠረ ግለሠብን መደበቅ ሆነ እንዲያመልጥ መተባበር የህግ ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ያስታውቃል።

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group