Translation is not possible.

ኪታባቸውን ተንተርሰው ለልጃቸው የገዙት ዳቦ በደማቸው ጨቅየቶ ዱንያን የተሰናበቱት ሸይኽ አብዱ ያሲን!

ሳኡዲ በነበሩበት ወቅት የሸህ ዑሰይሚን ደረሳ፣ ሱደይስን ተጅሪድ ያቀሩ ታላቅ ዓሊም ናቸው። ወደ ሀገር ከተመለሱ ወዲህ አፍንጮ በር በሚገኘው አቅሷ መስጅድ ያስቀሩ፣ በኋላም የአስኮ አዲስ ሰፈር በድር መስጂድ ኸጢብና ሸይኽ ነበሩ።

ትናንት ምሽት ኪታባቸውን ተንተርሰው የገዙት ዳቦ በደም ጨቅይቶ ከመሬቱ ወደቁ። ከመግሪብ እስከ ኢሻ ተፍሲር ሲያቀሩ ያውም ሱረቱ ዙመርን ሲያብራሩ አምሽተው ሁሌም እንደሚያደርጉት መስጂድ በር ላይ ሲዋክ የሚሸጠውን አይነ አዕማውን አረቡን ለመሸት ከመስጂዱ በር ላይ ቆሙ። አረቡ ሁሌም "ኡስታዝ አይጠብቁኝ ይሂዱ" ይላቸዋል። እሳቸው ግን እሺ አይሉም። ከኢሻ በኋላ ለአረቡ ምርኩዝ ናቸው። እንጀራ አይበላም ለሚሉት ልጃቸው ዳቦ ገዝተው አረቡን ቤቱ እየመሩ አስገብተው ነው ወደቤታቸው የሚገቡት።

ትናንትም ከአረቡ ጋር ወደቤታቸው በማቅናት ላይ ሳሉ መታጠፊያ አሳቻ ቦታ ላይ ከቅርብ ርቀት በተተኮሰ ሽጉጥ ከጀርባቸው በኩል ተመተው ሲወድቁ አረቡም ራሱን ስቶ ከመሬቱ ተዘረረ። በአካባቢው መብራት ጠፍቶ ስለነበር ማንነቱ ያልታወቀው ገዳይ የልቡን አድርሶ ከቦታው ተሰወረ።

እዳ ያስጭንቃቸዋል በሽማግሌዎችም የተሰጣቸው ጊዜም አጭር በመሆኑ ያሳስባቸው ነበር። የተወሰነውን ገንዘብ ተበድረው ከፍለው ቀሪውን ለመክፈል ቤታቸውን ለመሸጥ እንዳሰቡ ነገር ግን የበድር መስጂድ ጀመዓዎች ቤቱ ከመሸጡ በፊት ትላንት ፈጅር ላይ ለመስጂዱ ጀመአ ዛሬ እሁድ ገቢ ለማሰባሰብ እቅድ ተይዞ ነበር። ግና የአላህ ውሳኔ ቀደመ። በቅርብ ጊዜ ወደ አኺራ ወደተሻገረችው ባለቤታቸው ጉርብትና ተጓዙ። አላህ ይዘንላቸው።

ከቀብራቸው በፊት እዳ ለመክፈል እየተንቀሳቀሱ ያሉ ኮሚቴዎች አካውንት ከፍተው ሁሉም ሙስሊም እዳቸውን እንዲከፍል ጥሪ አቅርበዋል።

የአካውንት ስም:- ጀሚል ሁሴን ፣ ሲሩ ሀሰን እና አብዱ ዑስማን

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:- 1000592716309

via mahi mahisho

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group