Translation is not possible.

ወጣትነቴን አገኘሁ በናንተ ሰበብ፡፡ (ከሪም)

ክፍል 3

 ከዚህ በፊት ተመርምራ ሲህር እንዳለ በትዳሯ ላይ እንዳወቀች ነገረችኝ፡፡ ማነው እንደዚህ ያለሽ አልኳት ፡፡ አዳማ ሂዳ ነበር ምርመራ የተደረገላት አንድ ሰውዬ ሙስባሃ እየቆጠረ አውራ ጣቷን አይቶ ነው የነገራት፡፡ ለሱም የሰጣትን መድሃኒት ነገረችኝ፡፡ 

በህይወቴ ሰው መትቼ ቀርቶ ተቆጥቼ አላውቅም፡፡ እንዴት እንደተበሳጨሁ አላውቅም በጥፊ አጮልኳት እንዴት ጠንቋይ ጋር ትሄጃለሽ አልኳት፡፡ ሙስሊም ናቸው አለችኝ፡፡ አይደሉም አልኩ ተከራከርኳት ብዙ ነገሮችን ስጠቁማት ተጣልተን ስለነበር በግዜው ዝም ብትልም በሁለተኛው ቀን ይቅርታ አለች ተውበትም አደረገች፡፡ 

በዚህ መሃል ለኔ ሳትነግረኝ እናንተ ዘንድ ህክምና ጀምራ ነበር፡፡ በሷ ላይ በጣም የሚገርም ለውጥ አይባት ነበር፡፡ ፊት የሆነ ነገር ስላት ብስጭት የሚያደርጋት አሁን ትመክረኝ ጀመር፡፡ እኔ ላይ እያሾፈች ነው ብዬ መልሼ ላናድዳት ያልፈጠረብኝን አውቄ ሳናዳት እሷ በጣም ትረጋጋብኝ ነበር፡፡ በተለይ በጣም ስልኳ ላይ ግዜ ታሳልፈፋለች፡፡ 

በሌላ ነገር እንዳልጠረጥራት ደግሞ ማታ ላይ ኪታብ ትቀራለች ሰላቷን ትሰግዳለች፡፡ ግንኙነት ላይ እንደበፊቱ አታስጨንቀኝም በፍቅር ነው የምናደርገው፡፡ በፊት  እኔ መውለድ እፈልጋለሁ ነበር ጭቅጭቃችን አሁን ግን ናፍቀሀኛል ትለኝ ጀመረ፡፡

 የሆነ ሰው መክራት ነው ብዬ በጣም ገርሞኝ ትቼዋለሁ፡፡ አሁን የሆነ ቀን ህልም አየች በጣም ያስጨነቃትን ህልም ፡፡ እና ስለዛ ህልም ነግራኛለች፡፡ ኅልሙ እኔንም በጣም አስገርሞኝ ስለነበር በውስጤ ይዤዋለሁ፡፡

 ከዛንም በነጋታው ይሁን ብቻ አላስታውስም እኔ ሸሚዜን እየተኮስኩ እያለ ስለ ህልሟ አስታወሰችኝና ሰደቃ ብትሰጥ ግን የተሸለ ነው፡፡ አለች፡፡ እኔ ሰደቃ እሰጣለሁ ምንም ያጎደልኩት ነገር የለም አልኳት፡፡ አቃለሁ ግን የምትሰጠውለሚያቃቅሙህ ሳይሆን በትክክለ ለሚፈልጉ ሰዎች ነው፡፡ ይቀጥላል፡፡

ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇

https://t.me/Qallbdoc

ህክምና ለማግኘት👇

https://t.me/freeeeeeeeeeeere

👆

ህክምና ለማግኘት👇

https://t.me/UstazulQallb

👆

Send as a message
Share on my page
Share in the group