Translation is not possible.

👉ዳሰሳ ጋዛ!

፨የጦርነቱ ግለት እየቀነሰ እየሄደ ነው ያለው ። የአየር ድብደባዎች ቢቀጥሉም የምድር ጦር ፍልሚያው ግን መቀነስ ያሳያል ። እስራኤል በእግር ጦር የመጓዝ ትግሏ ውጤት አለማስመዝገቡን ተከትሎ በርካታ ሰራዊቷን ከጋዛ አስወጥታለች ። እናም የተመረጡ ኢላማዎችን መደብደብን እና በልዩ የሰው ሀይል መዋጋትን አድስ ስልት አድርጋ ቀርባለች።

፨እስራኤል ሀማስን ማጥፋት እንደማትችል ዘግይታም ቢሆን ተረድታዋለች ። እናም አሁን የጦር ፉከራው "ሀማስን ከማጥፋት " ወደ " ሀማስን ማዳከም" ተሸጋግሯል ነገር ግን ይህም አሁን ባለው ሁኔታ እንኳን ሊሳካ እንደውም ሃማስን አይደግፉትም ይባሉ የነበሩት የዌስት ባንክ እና ራማላህ ወጣቶች በገፍ እየተቀላቀሉት ተስተውሏል።

፨የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት እስራል በየቀኑ 60 ወታደሮቿ ጉዳት እየደረሰባቸው ወደ ማገገሚያ ቦታ እየተላኩ ሲሆን እስካሁን 12,500 ወታደሮቹ የአካል ጉዳተኛ እንደሆኑበት ከነዚህም መካከል 2,300 ያህሉ ቋሚ የአካል ጉዳተኛ መሆናቸውን አሳውቋል። ሌሎች ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ ከሀማስ ጋር እየተደረገ ባለው ፍልሚያ በጦርነቱ እየተሳተፉ ከሚገኙት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የእስራኤል ጦር አባላት ውስጥ ከላይ የተገለፁት 12,500 የሚሆኑት ሁሉም እስከወዲያኛው የአካል ጉዳተኛ ሆነው ወደ እስራኤል መመለሳቸውን እየገለፁ ነው።

፨አሜሪካ የሀማስን የፋይናንስ ምንጮች ለጠቆመኝ የ 10 ሚሊዮን ዶላር ወሮታ እከፍላለሁ ብላለች ። አሜሪካ ይህን ያለቺው ትላንት ሲሆን የሀማስ የገንዘብ አቅምን ማዳከምን ኢላማ ባደረገ እንቅስቃሴዋ ነው የሀማስን የገንዘብ ምንጭ ለጠቆመኝ 10 ሚሊዮን ዶላር እሸልመዋለሁ ያለቺው።

፨የየመን ሁቲዎች ወደ እስራኤል በሚጓዙ መርከቦች ላይ የሚፈፅሙትን ጥቃት አጠናክረው ቀጥለዋል ። በዛሬው እለትም የሚሳኤል ጥቃት አድርሰዋል ። ይህንንም አሜሪካና አጋሮቿ ማስቆም አልቻሉም ። በመሆኑም Maerskን የመሳሰሉ የአለማችን ግዙፍ የመርከብ ተቋማት በቀይ ባህር የሚያደርጉትን ጉዞ ሙሉ በሙሉ ለጊዜው ማቋረጣቸውን አሳውቀዋል ። ይህም ግብፅን እና እስራኤልን በከፍተኛ ሁኔታ የሚጎዳ ይሆናል ።

፨ግጭቱ ከታሰበው በላይ ወደ ሶሪያ,ኢራቅ,,የመን እና ሊባኖስ መስፋፋቱን ተከትሎ በሁሉም ሀገራት የሚገኙ ኢስላማዊ ተቃውሚ ቡድኖች በእስራአኤል እና አሜሪካ ይዞታዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ቀጥለዋል እንዲሁም ትላንት በነበረ ውሎ እስራኤል በይፋ ከሂዝቦላህ ጋር በሰሜናዊ ሊባኖስ ውጊያ ስታደርግ ውላለች፡፡ በተጨማሪም በኢራቅ እና ሶሪያ የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች የጋዛ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ከ160 በላይ ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡

፨ጦርነቱ ቀጠናውን ወደ ለየለት ግጭት እንዳያስገባው በተሰጋበት በዚህ ወቅት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ነገሩን ለማብረድ ያለመ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ጉዞ ወደ መካከለኛው ምስራቅ የጀመሩ ሲሆን በጉዟቸው ግብፅ,ኳታር,ሳዑዲ አረቢያ, እስራኤል, ቱርክ, ግሪክ,ጆርዳን እና ዌስት ባንክን ይጎበኛሉ ከመሪዎች ጋርም ይወያያሉ፡፡

፨የጋዛ ነዋሪዎች ስቃይ ቀጥሏል ። ረሀብና ጥሙ ፤ በሽታና ሞቱ ተፈራርቆ ዓለምም በዝምታ እያያቸው ጋዛ ለነዋሪዎቿ የስቃይ እስር ቤት ሆና ቀጥላለች።

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

like, comment, share follow

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group