Translation is not possible.

,

ደጋግ ቀደምቶችና ወላጆቻቸው

بسم الله الرحمن الرحيم

🔥 ታላቁ ሶሀቢይ አቡ ሁረይራ (رضي الله عنه) ዘወትር ከቤቱ ሊወጣ ሲል ደጃፍ ላይ ይቆምና "እናቴ ሆይ‼️ የአሏህ ሰላም ፣ እዘነትና በረከት ባንቺ ላይ ይስፈን" ይላታል። እርሷም ባማረ መልኩ አፀፋውን ስትመልስለት አስለጥቆ "እናቴ ሆይ‼️ በህፃንነቴ በርህራሄ እንዳሳደግሽኝ አሏህ ይራራልሽ" ብሎ ዱዓ ሲያደርግላት "በትልቅነቴ እንደተንከባከብከኝ አሏህ ይዘንልህ" ብላ ትመልስለታለች። ወደ መኖሪያቸው ሲመለስም ይህንን ያማረ ምልልስ ከእናቱ ጋር ያደርጋል። አሏሁ አክበር‼️ ምንኛ ያማረ ፍቅር🔥

👌 ከዐሊይ ኢብን ሁሰይን እንደተዘገበውም ከእናቱ ጋር በአንድ ገበታ መብላትን በእጅጉ ይፈራ ይጠነቀቅም ነበር። ለዚህም ምክንያቱ ምን እንደሆነ ሲጠየቅ የሚከተለውን ልብን ሰብሮ ዐይንን ሚያስነባ መልስ ነበር የመለሰው። ዐሊይ ይናገራል "እኔ ይህን ማድረግ ማልፈልገው ድንገት የእናቴ አይን ባረፈበት የገበታው ምግብ ላይ እጄ ቀድሞ አርፎ ሀቋን እንዳላጓድል ስለምፈራ ነው።" ላ ኢላሀ ኢለሏህ🔥 ምን አይነት ጥንቃቄ ⁉️ ምንስ አይነት የአሏህ ፍራቻ⁉️

🔥 እኚህ ደግሞ ታላቁ ዓሊም ሚስዐር ብን ሀቢብ አልጂርሚይ ናቸው!! ከእለታት በአንዱ ሌሊት እናታቸው በሌሊቱ እኩሌታ ተነስታ ውሀ ያጠጣት ዘንድ ጠየቀችው። ሚስዐርም ውሀውን ይዘው ሲመጡ እንቅልፍ እናታቸውን እንዳሸነፈና እንዳሸለቡ አስተዋለ። ከዚያም ውሀውን እንደያዘ መባነናቸውን ሲጠባበቅ የንጋት አብሳሪው ጎህ ፈነጠቀ። እናታቸውም ውሀውን ሳይጎነጩ እርሳቸውም ከቦታው ፈቀቅ ሳይሉ ሌሊቱ ነጋ‼️ አሏሁል ሙስተዓን‼️ ያ አሏሏሏሏሏሏሏህ!! ምን ነበር እኚህ ጀግኖች ሲሰሩ የነበረው⁉️

🔥 ይህ ደግሞ ዐውን ቢን ዐብደሏህ ነው! በዛ እዝነትና ርህራሄ በተሞላው አንደበቷ እናቱ ጠራችው። እርሱም በቅጽበት ነበር "ለበይኪ ያዑማህ " ብሎ የመለሰላት። ነገር ግን ድምፁ ከእናቱ ድምፅ በላይ ከፍ ማለቱን ዘግይቶ ነበር ያስተዋለው። በዚህም ተግባሩ እጅጉን ተፀፀተ!! ሀቋን የማጓደል ስሜትም ስለተሰማው የተግባሩ መካሻ ይሆን ዘንዳ ሁለት ባሮችን በአሏህ መንገድ ላይ ነጻ አደረገ‼️

ያ አሏህ!! ምን አይነት ትውልድ ይሁን ያለፈው⁉️ እስኪ እናስተንትን ውዶች🛎 ይህ ግለሰብ የነበረውንና እኛ ተላሎቹ ከወላጆቻችን ጋር ያለንን መስተጋብር 💔 ተውት ድምፅ ከፍ ማድረጉን እኛ ሙስሊሞቹ አይደለን እንዴ ወላጆቻችንን ማመናጨቅ መሳደብ የዘወትር መገለጫችን የሆነው⁉️ አለፍ ሲልም እስከ መደብደብና ግድያ ድረስ ያሉ ከተራራ የገዘፉ ሀጥያቶችን እየተገበርን ያለነው ⁉️ ያአሏህ አንተው ሁነን🤲

💔 ቀደምቶቻችንስ ቢሆኑ ከበስተኋላቸው በሚመጡት ላይ ጉዳዩን ምንኛ አከበዱት⁉️ እኛንስ አሁን ያለንበትን ሁኔታ ቢያዩ ምን ይሉ ይሆን⁉️ ... ነገር ግን አሏህ ሁሉንም አይቷል፤ ያያልም‼️

አሏህ የቀደምቶቻችንን ያህል ባይሆንኳ የወላጆቻችንን ሀቅ ለመጠበቅ የምንጥር ባሮች ያድርገን🤲🤲

رَبَّنَا ظَلَمۡنَآ أَنفُسَنَا وَإِن لَّمۡ تَغۡفِرۡ لَنَا وَتَرۡحَمۡنَا لَنَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ🤲🤲

✍ Abu remzan Asselefy

Send as a message
Share on my page
Share in the group