Translation is not possible.

እግሮችን ወደ ቂብላ አቅጣጫ መዘርጋት

~

ከዑለማእ ውስጥ እግሮችን ወደ ቂብላ አቅጣጫ መዘርጋትን የተጠላ ነው ያሉ አሉ። ነገር ግን ይህንን የሚከለክል አንድም ማስረጃ የለም። ሸይኽ ኢብኑ ሑመይድ - ረሒመሁላህ - "ከዚህ የሚከለክል የለም" ይላሉ። [ፈታወ ሸይኽ ኢብኒ ሑመይድ: 144]

ሸይኽ ኢብኑ ባዝም እንዲሁ ምንም ችግር የለበትም ብለዋል።

ኢብኑ ዑሠይሚንም እግሮችን በእንቅልፍ ጊዜ ወደ ቂብላ አቅጣጫ ስለማድረግ ሲጠየቁ እንዲህ ብለዋል፦

ليس على الإنسان حرج إذا نام ورجلاه في اتجاه القبلة .

"በአንድ ሰው ላይ እግሮቹ ወደ ቂብላ አቅጣጫ ሆነው ቢተኛ ችግር የለበትም።" [ፈታወ ሸይኽ ኢብኒ ዑሠይሚን፡ 2/976]

Ibnu Munewor

=

የቴሌግራም ቻናል፡-

https://t.me/IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

كناشة ابن منور
Send as a message
Share on my page
Share in the group