Translation is not possible.

መውሊድ በዩኔስኮ ቢመዘገብ እንኳ ከቢድዓነቱ አይወጣም‼

========================================

✍ የዲን አካል የሆነ ነገር የሚደነገገው በወሕይ (ቁርኣንና ሐዲሥ) እንጂ ዩኔስኮ ላይ በመመዝገብ አይደለም።

ይልቅ ቢድዓህን ለማንገስ በድብቅና በይፋ የሚጣጣሩ አካላት ቢቆጠቡና ሱንና ላይ ቢበረቱ ብዙ ባተረፉ ነበር።

ሐላልና ሐራም የሚወሰነው ዩኔስኮ ላይ በመመዝገብና ባለመመዝገብ አይደለም። በመሠረቱ ማስረጃ የሌለው ነገር በየትኛውም መልኩ ቢጠጋገን ዋጋ የለውም። «መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ!» እንዲሉ ነው ነገሩ።

አብዛሃኛውን ጊዜ ሙስሊም ጠል ወገኖች የሚረባረቡት ሁሉንም ሙስሊም በሚጠቅመውና በሚያስማማው ጉዳይ ላይ ሳይሆን በሚከፋፍለው አጀንዳ ላይ ነው። በእንዲህ አይነት ከፋፋይ ጉዳዮች ላይ እጃቸውን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እያስገቡ ክፍፍሉን ያባብሱታል፣ ቤንዚን ያርከፈክፉበታል።

20 ካሬ መሬት ለመስጅድ ስጡ ሲባሉ ግን ያንገሸግሻቸዋል።

እንዳውም የመስጅድ ቦታ የሆነውን እየተቃወሙ ያግዳሉ። ሩቅ ሳንሄድ ሰሞኑን እንኳ አንድ የፓርላማ አባል ፓስተር አዛን መስማት አልፈልግም አለ ተብሎ ቅሬታው ተሰሚነት አግኝቶ ሺዎች ሊገለገሉበት የሚችልን መስጅድ አግደዋል።

||

t.me/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group