Translation is not possible.

እኛስ_በ20_አመታችን❓

🔖#ዐምር ኢብን ሰለማ ገና በ7 አመቱ ቁርኣን በመሀፈዙ ብቻ ታላላቅ ሰሐቦችን ጭምር #ያሰግድ ነበር።

🔖#አብደላህ ኢብኑ አባስ ነብዩን እግር በእግር እየተከተለ በሄዱበት አብሯቸው እየሄደ "#ጌታዬ ሆይ በዲን ውስጥ አዋቂ አድርገው የነገሮችንም ፍቺ #አሣውቀው\" የሚለውን ዱዓ ከሳቸው ሲወስድ ገና የ13 አመት #ታዳጊ ነበር።

🔖#ነብዩላህ ኢብራሂም የሙሽሪኮችን #ጣዖቶች ሲጨፈጭፋና ተይዘው ወደ እሳት ሲወረወሩ 16 #አመታቸው ነበር።

🔖ነብዩ #ኢስማኤል የአባቱን የነብዩላህ ኢብራሂምን እና የጌታውን ቃል #በማክበር እንደ በግ ለመስዋትነት #ሲጋደም 15 አመት አልሞላውም ነበር።

🔖#ኡሳማ ኢብን ዘይድ በ18 አመቱ እነ አቡበክርን ጨምሮ ታላላቅ ሰሀቦች የነበሩበትን #ጦር እንዲመራ በረሱል ሰለላሁ ዐለይህ ወሰለም #ተሾመ።

🔖#ሙዓዝ ኢብን ጀበል ገና በ20 አመቱ ለኢስላም ተልዕኮ ወደ የመን #በአምባሳደርነት ተላከ።

🔖#አስማዕ ቢንት አቡበክር አስሲዲቅ ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ  ወሰለም እና አባቷ #ከቁረይሾች በዋሻ ውስጥ በተደበቁ ጊዜ በየቀኑ 5 ኪሜ ያህል #ተጉዛ ስንቅ ስታመላልስ ገና የ23 አመት ኮረዳና የ7 ወር ነፍሰ #ጡር ነበረች።

🔖#ሰዐድ ኢብን ሙዓዝ በ30 አመት ሰልሞ ለ7 አመታት ብቻ በእስልምና ኖረ ሲሞት ግን #የአርረህማን ዐርሽ ተንቀጠቀጠለት። ምን #ቢሰራ ነው❓

🔖#ኢማም አሻፊዒ ገና በ6 አመታቸው ቁርኣንን #ሀፈዙ በ15 አመታቸው #ሙፍቲ ሆኑ።

#አሁን አኔ አንተ አንቺ #ባለንበት የእድሜ ደረጃ #በኢላለማዊ ዕውቀታችን #በኢስላማዊ እሴታችን እውን በተግባሮቻችን ለኢስላም በመስራት እውን #ኢስላም ከኛ የሚፈልገውን ያህል ሰርተናልን?! #ፍርዱን ለህሊናችን እንስጠው #ወዳጆቼ!

https://t.me/furqan_school

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group