Translation is not possible.

አስገራሚ ታሪክ ነው

#ሼር_ማድረግ_እንዳይረሱ

ፍትህ እና ፍርድ በጀሊሉ ችሎት...

-----------**-----------

✅✅ሙሳ (ዐ.ሰ) አንድ ቀን ከአላህ ጋር እያወራ ሳለ አላህን እንዲህ ብሎ ጠየቀው፦ "ጌታዬ እስቲ ያንተን ፍትህ እና ያንተን ፍርድ አሳየኝ?"

አላህም፦ "አንተ እኮ ችኩል እና ማትታገስ ነህ እንዴት አድርጌ ላሳይህ" ብሎ መለሰለት።

ሙሳም፦ "ባንተ እገዛ ትዕግስት አደርጋለሁ" አለው።

አላህም፦ "እንዲህእንዲህ ... የሚባል ቦታ የውሀ ምንጭ አለ። እዛች ቦታ ማንም እንዳያይህ ተደብቀህ ችሎታዬንና ውስጥ አዋቂነቴን ዝም ብለህ ተከታተል" አለው። ሙሳም (ዐ.ሰ) እዛች ምንጭ ጋ ደረሰና ምንጯ አጠገብ ማንም በማያየው መልኩ እንዲት ዛፍ ላይ ወጥቶ ቁጭ አለ። ከዚያም አንድ ፈረሰኛ ምንጯ ጋ መጣና ፈረሱን አቁሞ ውሀ ጠጣ። በዛውም በአንድ ከረጢት 1000 ዲናር አጠገቡ አስቀመጠና ትንሽ ጋደም አለ።

ከትንሽ እረፍት በኋላ ፈረሰኛው ያስቀመጠውን 1000 ዲናር ረስቶ ጉዞውን ጀመረ። ይህ ሁሉ ሲሆን ሙሳ በትኩረት እየተከታተለ ነው። ብዙም ሳይቆይ አንድ ልጅ መጣና ከምንጩ ጠጣና ሊሄድ ሲል ያ ፈረሰኛ ረስቶ የሄደውን 1000 ዲናር አየ። በጣም ተደስቶ ይዞት ሄደ። ከዚያም ልክ ልጁ አከባቢውን ለቆ እንደሄደ አንድ ማየት የተሳነው ሽማግሌ መጣ።

ከምንጩ ጠጥቶ ውዱእ አደረገና እዛው ሰግዶ ጋደም አለ። ልክ ይህ ሽማግሌ ጋደም እንደዳ ያ የቅድሙ ፈረሰኛ ዲናሩን አስታውሶ ሲጋልብ መጣ። ቦታው ላይ ሲደርስ ሽማግሌው ተኝቷል ፈረሰኛውም ሽማግሌውን ቀሰቀሰውና፦ "አሁን እዚህ ጋ ውሀ ጠጥቼ 1000 ዲናር ረስቼ ሄጃለሁ። ካንተ ሌላ ማንም እዚጋ አልመጣም ስለዚህ ንብረቴን አሁን አምጣ" አለው። ሽማግሌውም፦ "ልጄ እኔ እንደምታየኝ እውር ነኝ ምንም ማየት አልችልም ታዲያ እንዴት አድርጌ እወስዳለሁ?" አለው። ፈረሰኛውም በጣም ተናደደ እየዋሸውም እንደሆነ ገመተ።

ከዚያ ጎራዴውን አወጣና፦ "ንብረቴን ምትመልስ ከሆነ መልስ አይ ካልክ በዚህ ሆድህን እተረትረዋለሁ" ሲለው... ሽማግሌው ማልቀስ ጀመረ።

ሙሳ (ዐ.ሰ) ይህን ሁሉ በትዕግስት እየተከታተለ ነው፡፡ ትዕግስቱ ሲሟጠጥ የጌታውን ቃል በማስታወስ ባለበት ይፀናል። ከዛ ፈረሰኛውም በያዘው ጎራዴ የሽማግሌውን አንገቱን ቀነጠሰለት። ከዚያም ልብሱን አገለባብጦ ሲፈትሽ ምንም ሊያገኝ አልቻለምና ትቶት ሄደ። ከዚያም አለህም እንዲህ አለ፦ " አንተ ሙሳ ይህ የኔ ፍትህ እና የኔ ፍርድ ነው፡፡"

ሙሳም፦ "ጌታዬ ትዕግስቴ ተሟጥጦ አልቋል አንተ ጥበበኛ ነህ እስቲ አስረዳኝ" አለው አላህም፦ "እኔ ውስጥ አዋቂ ነኝ አንተ የማታውቀውን አውቃለሁ።

1⃣ ቅድም መጥቶ የፈረሰኛውን ንብረት የወሰደው ልጅ የራሱን ሀቅ ነው የወሰደው። ምክንያቱም የልጁ አባት! እዛ ፈረሰኛው ዘንድ ተቀጥሮ ሰርቷል ፈረሰኛውም የላቡን ከልክሎታል። ስለዚህ ልጁ የወሰደው የአባቱን ሀቅ ነው።

2⃣. "እውሩ ሽማግሌ ደሞ ድሮ አይኑ ከመጥፋቱ በፊት የዛን ፈረሰኛ አባት ገድሎት ስለነበር። ፈረሰኛው የአባቱን ገዳይ እንዲበቀልለት አድርገናል።

"ያ ሙሳ! ለሁሉም ሀቁን አድርሰናል። አንዱ ፍትሀችን ሲሆን አንዱ ደሞ ፍርዳችን ነው። እኛም የጥበበኞች ሁሉ ጥበበኛ ነን አለው።

አጂብ ... ሱብሀን አላህ!!!

  🕋ላኢላሀ ኢለላህ ሙሀመዱን ረሱሉሏህ☝

"ወደ መልካም ነገር  ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

ሼር፦ @fafiru_illahi

Send as a message
Share on my page
Share in the group