Перевод невозможен

ጋዛ፥ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች መራባቸውን ተመድ ገለጸ

ጋዛ ሰርጥ ውስጥ 2,2 ሚሊዮን ሰዎች «ለረሐብ አደጋ» ተጋልጠዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) አስጠነቀቀ ። በርካታ ርዳታ ለጋሽ ድርጅቶችም ጋዛ ውስጥ ያለው ሁኔታ «በዓለም ምሳሌ የሌለው» ነው ሲሉ አዲስ ባወጡት ጥናት ገልጸዋል ።  የእሥራኤል ጦር የአየር እና የምድር ጥቃት ዘመቻ ባጠናከረባት ብሎም ከበባ ውስጥ ባለችው ጋዛ የርዳታ ምግብ ማስገባት ባለመቻሉም ግማሽ ሚሊዮን ሰው መራቡን ተመድ ዘግቧል ።  በዋናነት ፍልስጥኤማውያን በሚኖሩበት የጋዛ ሰርጥ ውስጥ 576.600 ሰዎች ቀድሞውኑም ተርበዋል ሲል ተመድ ዐስታውቋል ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የምግብ መርኃ ግብር ዋና የምጣኔ ሐብት ባለሞያ አሪፍ ሑሴይን ከጋዛ ነዋሪዎች አንድ አራተኛው መራቡን ተናግረዋል ።

«ዘገባው ብርቱ ሥጋታችንን የሚያረጋግጥ ነው ። ጋዛ ውስጥ ሁሉም ሰው በሚባል ደረጃ የተራበበት ሁኔታ እንዳለ ነው የሚያሳየው ። ከ500 ሺህ በላይ፤ ግማሽ ሚሊዮን ሰዎች ተርበዋል ። ያ ማለት፦ አሁን በምንናገርበት ቅጽበት ከጋዛ አራት ነዋሪዎች አንዱ እየተራበ ነው ።»

ቁጥራቸው 23 የሚደርስ የተመድ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ሌሎች የርዳታ ድርጅቶችም በጋራ ባቀረቡት የጥናት ውጤት መሠረት፦ ከሚደርሰው ጥፋት ባሻገር የጋዛ ነዋሪዎችን «ረሐብ እና በሽታም» እያሰቃያቸው ነው ።

እነሱ ተረስተው ችግሩ በርትቶባቸዋል።ዛሬም እስራኤል በደሏን ቀጥላ ሰዎቹ እንዲሰደዱ አዛለች።

አላህ ነስሩን ያርብላችሁ ያረብ 🤲

Отправить как сообщение
Поделиться на моей странице
Поделиться в группе