Translation is not possible.

🔰 ያለ ምላሽ

የሳር ድርቆሽ ውስጥ መርፌ (💉) የመፈለግን ያህል ከባድ ነገር የለም፤ ነገር ግን ከውስጣችን ፍላጎት ካለንና ጥረት ካደረግን በሳር ድርቆሽ ውስጥ እኳን ቢሆን መርፌውን እናገኘዋለን።

አንድ ነገርም ጠንቅቀን እናውቃለን መርፌውን በምንፈልግ ወቅት መርፌው ሊጎዳን እንደ ሚችል። ይህ ሁሉ ሆኖም ተባብረን፣ ከውስጣችን ፍላጎት ኖሮና ጥረት ከታከለበት መርፌው ሳይጎዳንም ልናገኘው እንችላለን።

ይህን የምናውቀው መርፌውን በሳር ድርቆሽ ውስጥ እናገኘዋለን ብለን በሙሉ እምነት ስንፈልግ ብቻ ነው።

የትኛውም ነገር ጥረት ይጠይቃል።

➻ይህ ጥረታችን ብዙ የሆኑ እኛን ሊፈታተኑን የሚችሉ እንቅፋቶችም ሊኖሩት ይችላሉ ነገር ግን ጥረታችን ከጧጧፍነውና ብዙ ሆነን በአንድነት ከተባበርን ምንም ያህል የህይወት ጉዞአችን ከገለባው ያልተለየ እንክርዳድ ቢበዛበት፤ አብሮነታችንና ቅንነታችን እነዚህን እንቅፋቶች የመቋቋም ኃይል ይኖረዋል።

ጠንካሮች ሆነን በአንድነት እንዲሳካልን የፈለግን እንደሆነ ብዙ ጥንካሬን የሚሹ ጥረቶችን ማድረግ ይኖርብናል።

➻ ጥንካሬን ከሚሹ ሲታዩ ግን ቀላል ከሚመስሉ ነገሮች ብንጀምር......

ያለ ምላሽ ማፍቀርን

ያለ ምላሽ ደግ መሆንን

ያለ ምላሽ ሰዎችን ማገዝና መርዳትን

ያለ ምላሽ ማገልገልን

ያለ ምላሽ ሰዎችን ማክበር

ያለ ምላሽ ሰዎችን መውደድን ልማዳችንና ማንነታችን ማድረግ‼️

አዎ እንደ መልካም ስራ ጥንካሬን የሚፈትን ምን ነገር አለ?

-  እየተጠሉ መወደድ፤

- እየተዋረዱ ክብር መስጠት፤

- በጥላቻ መንፈስ እየታዩ ፍቅርን መስጠት

- እየተገፉ አለሁኝ ማለት፤ ጠንካራ ማንነትን ይጠይቃል። ይህ ጠንካራ ማንነት ደግሞ ከየትም አይመጣም ከኛው ድግግሞሽ ያለበት ሙከራና ጥረት ነው።

⛔ ትዕግስትን አንደ ፍርሃት፣

⛔  ይቅር ባይነት እንደ ውርደት፣

⛔  አክብሮት እንደ ማስመሰል የሚቆጥሩ ሰዎች ብዙ ናቸውና የነሱን ተቃውሞ፣ ዛቻና ትችት የሚችል አቅም መገንባት ይኖርብናል። ይህ አቅም ደግሞ የሚመጣው ምንንም ነገር ያለ ምላሽ ስናደርግ፤ ድርቆሽ ላይ መርፌ የመፈለግን ያህል ከባድ ነገሮችን በአንድነት ስንደፍር ነው!!

በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

tiktok.com/@sharpswords1

https://t.me/SharpSwords1

www.youtube.com/@SharpSwords1

Instagram.com/sharp_swords1

https://ummalife.com/ReshadMuzemil

Send as a message
Share on my page
Share in the group