Translation is not possible.

ምልክት ነኝ እኔ!

«ዘውድአለም ታደሠ» (2019G.C)

ማፍረስን ያውቃሉ

መጠገን ታውቃለህ

መግደልን ያውቃሉ

ማዳን ትችላለህ

አንተን ያመነች ነፍስ ፥ መቼ ትተዋለህ?

“እሳት ከላይ ዘንቦ፥

ህንፃ እያፈረሰ ፥ ነፍስ እየቀጠፈ

ከቶ በምን ታምር ፥ ሳይነካኝ አለፈ?”

ብዬ አልጠይቅም!

ከሃያላን ሁሉ የሚልቀው ሃያል

ከፍርስራሽ መሃል

ደካማ ታድጎ ፥ ጉልበቱን ያሳያል!

እሳት የሚተፋው

በራሪ እንዳሞራ

ሞት እየተኮሰ

መስኪድ እያጋየ

ቢፎክር ቢያቅራራ

ጡንቻውን ቢለካ ፥ ተራራ እየናደ

አንድ ነፍስ አትጠፋም ፥ አላህ ካልፈቀደ!

እንዲህ ነው ሚናገር ጀሊሉ በቅኔ

ሁሉን እንደሚችል ፥ ምልክት ነኝ እኔ!

ዱንያ እንደው ከንቱ

እንፋሎት ነች ጤዛ

ሁኔታን እያየሁ ፥ ለምን ሃዘን ላብዛ?

ብሞትም ጀነት ነኝ ፥ ብኖርም በቅፉ

የሱን ቅጥር አልፎ ፥ አይነካኝም ክፉ!

ይልቅ አመዱ ላይ

ምንጣፌን ዘርግቼ

የዙሪያዬን ሳይሆን ፥ ሰማዩን አይቼ

ፈፅሞ ሳልፈራ ፥ ላንዲቷ ህይወቴ

እንበረከካለሁ ፥ እነሆ ሶላቴ!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group