Translation is not possible.

#ወንዶችም_3_አይነቶች_ናቸው_ብለዋል_2ኛው_ኸሊፋ ዑመር ቢን ኸጧብ رضي الله عنه

አንደኛው: ቁጥብ እና ጥንቁቅ የሆነ፣ አስተዋትና ብልህ፣ ገራገርና ተግባቢ፣ በማንኛውም ጉዳይ ላይ የራሱን ቆራጥ ዉሳኔ የሚወስን፣ ግራ የሚያጋቡና የሚያሻሙ ነገራቶችን ለመጋፈጥ የሚያስችለው ድፍረት፣ ወኔና ብልሃት ያለው ወንድ ነው።

2ኛው የወንዶች አይነት ቁጥብ የሆነ ሙስሊም ነው። አሰጊና አሻሚ ጉዳዮች ሲያጋጥሙት ግን በራሱ መወጣት አይችልም። ቆራጥ ዉሳኔ ለማሳለፍና ፊትለፊት ለመጋፈጥ ብልሀቱም ድፍረቱም የለውም። (ባይሆን ግን ኧረ እንድህ አይነት አሻሚ ጉዳይ አጋጥሞኝ ግራ ገብቶኛል፣ እባክህ ምን ላድርግ፣ ይሄን ችግር በምን መልኩ ልወጣው ብሎ ልምድና እውቀት ያለውን ሰው ያማክራል።) የተሰጠውን ምክር ተቀብሎ ተግባር ላይ ያውላል።

3ኛው ወንድ

ክፉና ጠማም፣ ግራ የተጋባ፣ ድንግርግሩ የወጣ፣ ወይ ከብልሃቱ ወይም ከድፍረቱ የሌለ፣ በራሱ የማይወስን፣ ሌሎች ሲመክሩትም የማይሰማ ለምንም የማይሆን አይነት ወንድ ነው።

"ሙሰነፍ ኢብኑ አቢ ሸይባ"

ወንድሞቼ

እኛስ ከየትኛው የወንዶች አይነት ነን ግን??

Send as a message
Share on my page
Share in the group