Translation is not possible.

አታለለሽ  አሉኝ ያ የዲን ነጋዴ፣

የዲን ካባ ለብሶ ተጠቅሞ ዘዴ፣

ግን!ሁሉም ነገር  ያልፋል  ቅር እዳይልሽ  ውዴ፣

የጎዳሽ  ሢመሥለው አስተምሮሽ ሄዴ፣

ለቀጣይ  አነቃሽ   ድርስ   ተወሰዴ፣

ሰለፍይ እህቴ አሰብኩኝ አርቄ፣

አስተገዘኝና መውደቅሽ መውደቄ፣

መልስሽን  ፈለኩኝ ለነዚህ ጥያቄ፣

ተቅዋ ካጣሽበትአሏህን ካልፈራ፣

በተሠጠው እውቀት ባወቀው ካልሰራ፣

ከኢልሙ ምን አለሽ ቢያሥተምር ቢያቀራ?

በጀነት ቢያበስር ከሳት ቢያሥፈራራ፣

ሰወችን ቢያነቃ በሌት በጠራራ፣

እራሡን ከረሳ ተግባሩ ካልጠራ፣

ከዳዕዋው ምን አለሽ ቢመክር ቢጣራ?

አደራ እህት አለም አጣሪ ተግባሩን፣

የአህላቁን ጉዳይ ውብ ሥነ ምግባሩን፣

አደራ እህት አለም ይቅርብሽ መቸኮል፣

እዳትጠለፊ  ባሥመሣዮች ተንኮል፣

ቢንት ሙሀመድ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group