የአሜሪካና ኢራን የቀይ ባህር ፍጥጫ
ታህሳስ 5/2016
በቴህራን የሚደገፉ የሃውቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር በሚጓዙ መርከቦች ላይ ጥቃት ማድረሳቸው ይታወሳል
የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ሞሀመድ ሬዛ አሽቲያኒ አሜሪካ በቀይባህር የሚጓዙ መርከቦችን ለመጠበቅ በሚል ከተለያዩ ሀገራት የሚውጣጣ ቡድን ለማዋቀው ማሰቧን አጥብቀው ተቃውመውታል።
ዋሽንግተንና አጋሮቿ ወደ ቀይባህር የጋራ ግብረሃይል ከላኩ “ከባድ ችግር” ይገጥማቸዋል ሲሉም አስጠንቅቀዋል
ሚኒስትሩ ኢስና ለተሰኘው የኢራን መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ማብራሪያ ቴህራን ስለምትወስደው እርምጃ ያሉት ነገር የለም።
“ማንም እኛ ከፍተኛ የበላይነት በያዝንበት ቀጠና መሰል እንቅስቃሴ ማድረግ አይችልም” ማለታቸው ተዘግቧል።
የአሜሪካ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫኒ ባለፈው ሳምንት አሜሪካ በቀይ ባህር የሚጓዙ መርከቦች ደህንነትን ለማስጠበቅ የሚረፋ የባህር ሃይል ወታደራዊ ግብረሃይል ለማቋቋም ከሌሎች ሀገራት ጋር ንግግር እያደረገች መሆኗን መግለጻቸው ይታወሳል።
ዋሽንግተን ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው በኢራን የሚደገፉ የየመን ሃውቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር በሚጓዙ መርከቦች ላይ የሚሳኤልና ድሮን ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ነው።
ለሃማስ አጋርነታቸውን የገለጹት የሃውቲ ታጣቂዎች እስራኤል በፍልስጤማውያን ላይ የምታደርሰውን ጥቃት ካላቆመች ከቴል አቪ ጋር ግንኙነት ባላቸው መርከቦች ላይ ጥቃት እንደሚያደርስ መዛቱ ይታወሳል።
ቡድኑ የየትኛውም ሀገር መርከብ ወደ እስራኤል የሚያቀና ከሆነ በሚሳኤል እመታዋለው ማለቱም አይዘነጋም።
ከወር በፊት የብሪታንያን መርከብ ያገቱት የሃውቲ ታጣቂዎች በቅርቡ የኖርዌይ ሰንደቅ አላማ የምታውለበልብ መርከብን በክሩዝ ሚሳኤል መምታቱም የአለማችን 10 በመቶ የንግድ መተላለፊያ የሆነውን ቀይ ባህር ውጥረት ውስጥ ከቶታል።
አሜሪካ እና ፈረንሳይም በቀይ ባህር ሊፈጸም ለሚችል ጥቃት የባህር ሃይላቸውን በተጠንቀቅ እንዲቆም ማድረጋቸውን ነው ሬውተርስ የዘገበው።
የሃውቲዎች ዛቻና ጥቃት እንዲሁም የዋሽንግተን የጋራ ወታደራዊ ግብረሃይል የማሰማራት ውጥን የእስራኤልና ሃማስ ጦርነትን አድማስ እንዳያሰፋው ተሰግቷል።
#ለወቅታዊና_እስላማዊ_ጉዳዮች
Join us
🇵🇸🇵🇸🇵🇸
https://t.me/Ihsan_media_1
https://ummalife.com/ihsan_midea
https://www.youtube.com/@ihsan_media1