Translation is not possible.

ሴቶች ሶስት አይነት ናቸው ይላል ዑመር ቢን ኸጧብ رضي الله عنه

አንደኛዋ- ገራገር፣ ምቹ፣ ቁጥብና ጥብቅ የሆነች ሙስሊም ሴት ነኝ። አፍቃሪም፣ ተፈቃሪም፣ ማህጸነ ለምለም የሆነች ሴት።

ባሏ ሲቸገር ከጎኑ የምትቆም፣ አብሽር ያልፋል እያለች የምታጠናክር፣ ይገባሃል፣ የእጂህን ነው ያገኘኸው፣ ደግ ሆነሃል፣ ኧረ ሲያንስህ ነው በማለት በመከራው ላይ ሌላን መከራ የማትደራርብ አይነት ሴት። የዚች አይነት ሴት በጣም ጥቂት ናቸውና ማግኘቱም ከባድ ነው።

2ኛዋ አይነት ሴት:

ቁጥብና ጥብቅ ሙስሊም ሴት ነች። ባይሆን ግን ልጅ ከመውለድ ያለፈ ምንም ሚና የላትም። (ይችም ለክፉ አትሰጥም።)

3ኛዋ ሴት

አመለ ክፉ መከራና ቅማል የሆነች ሴት ነች። ከራስ ላይ የማትወርድ፣ በአንገት ላይ የተጠመጠመች ማነቆ፣ በእጅ ላይ የገባች የመከራ ካቴና፣ ራቂ ቢሏት የማትርቅ፣ አብረሽ ኑሪ ብለው ቢተዋት ሰላም የማትሰጥ፣ አላህ ፈተናን ለፈለገበት ባሪያው የሚሰጣት፣ አላህ ካልሆነ በስተቀር የማያስወግዳት አይነት የፈተና ሸክም የሆነች ሴት።

{ሙሰነፍ ኢብኑ አቢ ሸይባ}

ከማንኛዋ ትሆኑ ይሆን?

Send as a message
Share on my page
Share in the group