Translation is not possible.

ባል እቤት ሲገባ ሚስቱ ስታለቅስ ያገኛትና ለምን እንደምታለቅስ ሲጠይቃት፦ "እዚህ ዛፍ ላይ ያለው አሞራ ያለ ሂጃብ ሆኜ ሲያየኝ ግዜ ወንጅል ሆኖ ታየኝ። ለዛ ነው ማለቅሰው" ብላ መለሰችለት።

ባልም በዚህ ቁጥብነቷ ተደስቶ እቅፍ አደረጋትና ግንባሯን ሳማት። ከዚያም ወዲያው መፍለጫ ይዞ ወጣ'ና አሞራው ሚያርፍበትን ዛፍ እንዳልነበረ አድርጎ ቆረጠው።

°

#እናላችሁ! ከዕለታት አንድ ቀን ባል ስራ በግዜ ጨርሶ ቤት ከች ሲል.... ያችን ቁጥቧን ሚስቱን ያችን አሞራ አየኝ ብላ ቂያማ ምታቆመውን ሚስቱን ከውሽማዋ ጋር ተኝታ ያገኛታል።

°

ምንም አላደረገም ትቶ ወጣ፣ወደ ሩቅ ሀገርም ሄደ። እና የሆነ ከተማ ሲገባ በጣም ብዙ ሰዎች እቤተ መንግስት በር ተሰብስበው ያገኛቸውና

ለምን እንደተሰበሰቡ ይጠይቃቸዋል። "የንጉሱ ወርቅ ማስቀመጫ ተዘርፎ ነው" ብለው መለሱለት።

°

በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ የሆነ ሰውዬ ጤነኛ/normal ነው ግን በእንብርክኩ ሲንፏቀቅ ያይና፦ "ይህ ሰው ለምን ቆሞ አይራመድም?" ብሎ ጠየቃቸው። እነሱም፦"አይ ይህማ የከተማችን ትልቅ ሸይኽ ነው በእግሩ ማይራመደው ምናልባት ሳያውቅ በእግሩ ጉንዳን እንዳይገድል ሰግቶ ነው" ብለው መለሱለት።

አአአአዎ በቃ እዝች'ጋ ተነቃቁ.....

ሰውየውም፦ "ወላሂ ሌባውን አገኘውት" ብሎ ጮኸ። ንጉሱም ጋ በፍጥበት ገባ'ና፦ "ያኛው ሸይኽ ተብዬ ነው ንብረትህን የሰረቀህ ከፈለግክ

አስፈትሸውና ውሸቴን ከሆን አንገቴን ቁረጠው" አለ። ወታደሮችም በንጉሱ ትዕዛዝ ሸይኽ ተብዬውን ፈትሸው እቃውን አገኙ።

ንጉሱም ለሰውዬው፦ "እንዴት ልታውቅ ቻልክ?" አለው። ሰውዬውም፦ "ቁጥብነት እና መልካምነትን እንዲህ [ድንበር ባለፈ ሁኔታ] ስታገኘው ከጀርባው ትልቅ ክህደት እንዳለ ያመላክታል" ብሎ መለሰለት።

የሚገባው ይገባዋል

ጆይን

https://t.me/SileTidarEnmekaker

Telegram: Contact @SileTidarEnmekaker

Telegram: Contact @SileTidarEnmekaker

ትዳር የአማኞች ምሽግ
Send as a message
Share on my page
Share in the group