Перевод невозможен

ይህንን ምስል በጥልቀት እየው። አይኖችህን ለትንሽ ሰከንድ ጨፍናቸው። ገለጥ አድርገህ መልሰህ በትኩረት ተመልከተው.... የተሰማህን ስሜት በልቦናህ ታቅፈህ እጅህን ወደ ሰማይ ከፍ አድርግ። ያ አላህ እርዳቸው አግዛቸው እያልክ በዱዓ አስታውሳቸው...

የጋዛው ሀምዛ ሙስጠፋ ምኞቱን እንዲህ ሲል ያወጋናል

"ለሰላሳ ደቂቃ ያለማቋረጥ መተኛት፣ አሁን ከምጠጣው ጥቁረቱ የቀነሰ አንድ ብርጭቆ ውሃ መጠጣት፣ ከተገኘ የሻገተ ቁራሽ ዳቦ በወቅቱ መመገብን በእጅጉ ናፍቄያለሁ። ንጹህ አየር መተንፈስ፣ ከምተኛበት መሬት በታች ወለሉ ላይ የሚዘረጋ አንሶላ ጨርቅ፣ ለሁለት ሳምንታት አካሌ ላይ የቆዩ ልብሶቼን መቀየር፣ ሚስትና ልጆቼን አቅፌ የምቀመጥበት ሰላማዊ መሬት ለቀናትም ቢሆን እመኛለሁ"

👇👇👇

ለፈጣን መረጃ ፔጃችንን ፎሎ አድርጋችሁ ተከተሉን

image
Отправить как сообщение
Поделиться на моей странице
Поделиться в группе