Translation is not possible.

ሙስሊም ማለት ጮሌ ነው‼

የሚጠቅመውንና የሚጎዳውን ጠንቅቆ ያውቃል።

ብልህ ከሆንክ መንገድ ላይ ሴት አፍጥጠህ አትመለከትም።

ለምን መሰለህ ሐቢቢ…

ስላየሃት ምን ታተርፋለህ? እሺ! አማረችህ እንበል። ስላፈጠጥክ ታገኛታለህ? በጭራሽ!

የምታገኘው ብቸኛ "ትርፍ" ምን እንደሆነ ታውቃለህ?

ወንጀል!

አንድ ሴት አተኩረህ ስታይ የሆነች ያክል ጥቁር ነጥብ ልብህ ላይ ጠብ ትደረጋለች። ካልቶበትክ ሌላም ጊዜ ስትመለከት ተጨማሪ ጥቁር ነጥብ ልብህ ላይ ይጨመራል። እያለ እያለ ሙሉ ቀልብህ በጥቁር ነጥቦች ይሸፈንና የፈለገውን ያክል ግሳፄ ቢሰማ ምንም የማይመስለው ደረቅ ይሆናል።

ቁርኣኑንም ስትሰማ ከጆሮህ አልፎ ወደ ቀልብህ አይንቆረቆርም። በወንጀል አጥር ተዘግቷላ! በየት ብሎ ይለፍ!

መፍትሄው ምን መሰለህ? በሐላሉ ማግባት። አንዳንዱ ደግሞ ጭራሽ አግብቶ የሚብስበት ልክፍት ነገር ነው። ይሄ እንኳን 4 ሴት 40 ሴት ቢደረደርም ክፉ አመሉ የሚለቀው አይመስልም።

ካገባህ ኸላስ ነገሩ አለቀ። ውጭ የምታፈጥባትም ሴት ናት። ያገባሃትም ሴት ናት። እዛች ጋ ያለው እዚህችም ጋ አለ። ሴት ሁሉ አንድ አይደለም ካልክ ደግሞ፤ ከመንቀዥቀዥ ታዲያ መጀመሪያውኑ አይተህ ባገባህ! አሁን ምን ያንቀዋልልሃል? እ¿ አቅሙ ካለህና መስፈርት ካሟላህ ደግሞ ድገም። ከዚያ ውጭ ግን አትልከስከስ!

አሊያ አንገትህን ቆልምመህ አላፊ አግዳሚዋን ስትመለከት ወይ መኪና ወይ ጋሪ ይገጭህና ከሁሉም ሳትሆን ትቀራለህ።

በቃ! መጀመሪያ ቀልብህን ሰትረው። ባለህ ተብቃቃ። የማታገኘውን አትመኝ። ብልጥ ሁን። ለማንም ብለህ ሳይሆን ለራስህ ስትል። አላህ ጋር ከተጣላህ፤ አለቀልህ።

አላህ ያዘዘህ ዓይንህን ስበር ብሎ ነው። ልብህ ወንጀሏ ተከምሮ በዝቶ በአፉ የተደፋ ኩባያ እንዳትሆን ፍራ። በአፉ የተደፋ ኩባያ የፈለገ ውሃ ብታደርግበት አይቀበልም።

አላህ እንዲህ ብሏል፦

(قُل لِّلْمُؤْمِنِينَ يَغُضُّوا مِنْ أَبْصَارِهِمْ وَيَحْفَظُوا فُرُوجَهُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَزْكَىٰ لَهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا يَصْنَعُونَ)

«ለምእመናን ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን (ያልተፈቀደን ከማየት) ይከልክሉ፤ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፤ ይህ ለነሱ የተሻለ ነው፤ አላህ በሚሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡»

[አንኑር: 30]

«ሙእሚን» የሚለው ቃል የሚመለከተኝ ሙስሊም ነኝ ብለህ ካመንክ፤ የጌታህን ትዕዛዝ ተቀበልና እይታህን ስበር። አላህ ያግዝህ፤ ያግዘን።

||

t.me/MuradTadesse

Send as a message
Share on my page
Share in the group