Translation is not possible.

🕰እንዲህ ነበሩ

.

📌ቡኻሪ ‹ለኢሕቲላም /አካለ መጠን/ ከደረስኩበት ጊዜ ጀምሮ ውሸት ወጥቶኝ አያውቅም፡፡› ብለዋል፡፡

.

📌 ሻፊዒይ ‹በውሸትም ይሁን በእውነት በአላህ ሥም ምዬ አላውቅም፡፡› ይላሉ፡፡

📌 ሰዒድ ኢብኑ አልሙሰየብ ‹አርባ አመት ሙሉ ሙአዚኑ አዛን ሲል መስጊድ ውስጥ ሆኜ ነው፡፡  ከኢማሙ ጋር ተክቢረተል ኢሕራም /የሰላት መግቢያ ተክቢራ/ አምልጦኝ አያውቅም፡፡› ብለዋል ፡፡

.

📌 በጀነት የተመሠከረላቸው አቡበክር አስስዲቅ ‹አንድ እግሬን ጀነት ውስጥ ባስገባ እንኳ የአላህን ውሣኔ አላውቅም፡፡› ይላል፡፡

.

📌‹ኢብኑ ዑመርን መንገደኛ ሆኖ ሲፆም በሀገር እያለ ደግሞ ከዒባዳው ሲሠንፍ አይቼው አላውቅም፡፡› ብለዋል ዓኢሻ፡፡

.

ይኸው በጠዋት ወጣን።

ቁምነገሩ መውጣትና መግባት አይደለም። አትርፎ መግባት እንጂ።  ምድር ላይ አሻራ ጥሎ ማለፍ እንጂ።

አምላኬ ሆይ በውሎዬ ቅናቻዬን አመላክተኝ። ከነፍሴ ክፋትም ጠብቀኝ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group