Translation is not possible.

የአልቀሳም ብርጌድ ቃል አቀባይ አቡ ዑበይዳ ዛሬ በሰጠው መግለጫ "ጉዳዩ የጥንካሬና የብዛት አይደለም" በማለት ንግግሩን ይጀምራል።

የናዚ ጽዮናውያን በሕዝባችን ላይ እየፈጸመ ያለውን አረመኔያዊ ጥቃት ቀጥሏል። ጦር ሜዳ የሚደርስበትን ኪሳራ ለመሸፈን በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተለይም ሴቶችና ሕጻናትን በጭፍን የበቀል እርምጃ እየወሰደ ይገኛል።

ባለፉት አስር ቀናት በአካባቢው የሰፈሩትን የጠላት ጦር ተጋፍጠን 180 ተሽከርካሪዎችን ሙሉ በሙሉና በከፊል ማውደም ችለዋል።

ሙጃሂዶቻችን በአል-ያሲን 105፣ የስትሮብና በታንዶም ሚሳኤሎች የጽዮናዊያኑን ተሽከርካሪዎች ማውደማቸውን ቀጥለዋል። በዚህ ኦፕሬሽን ብዙ የጠላት ጦርን ገለው አብዛኞቹ ሙጃሂዶቻችን በሰላም ተመልሰዋል።

ጠላት በጋዛ ሰርጥ በሰሜንና በደቡብ ያደረገው ዘመቻ አልተሳካለትም ወደፊትም አይሳካለትምም። ጥቃቱን ቀጥሎ ከጋዛ ሰርጥ ወደሌሎች አካባቢዎች ከተንቀሳቀሰ ይበልጥ ኪሳራውን ይከናነባል።

እርቁ ቅንነታችንን አረጋግጧል። በምላሹ የጠላቶቻችን አመራሮች ወታደራዊና ፖለቲካዊ ቃል አቀባዮች ዋሽተዋል።

ሙጃሂዶችንን የማስወገድ የጠላትን ተደጋጋሚ ጉራ ለንግግር ፍጆታ እንጂ በተግባር እንደማይሳካ አሳይተናል። አሳዛኝ ሽንፈቶቹ የመጨረሻው ክስተት በእየሩሳሌም መሃልና አካባቢዋ ተረጋግጧል።

ከጦርነቱ መጀመሪያ አንስቶ በተናገርነው ቅድመ ሁኔታ ካልሆነ በቀር አንድም እስረኛ አይፈታም።

ፅዮናዊቷም ሆነች የእርሷ ደጋፊና ተባባሪዎች ያለ ድርድርና ያለኛ ፈቃድ እስረኞቻቸውን በህይወት ሊወስዱ አይችሉም።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group