Translation is not possible.

#ኢብኑ_ጀውዚይ ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላሉ :-

አንድ ቀን መስጅድ ውስጥ ተኝቼ እያለ ጀናዛ ሊሰገድበት ይዘው ሲገቡ ድምፅ ሰምቼ ነቃሁ።

ልስገድ ብዬ ተነሳሁ ሰገድኩ ወደ ቀብር ይዘውት ሲሄዱም መሆድ አለብኝ ብዬ አብሬኛቸው ሄድኩ። ይህን ሁሉ ሳደርግ ሟቹን ጭራሽ አላቀውም ነበር።

ሰዎች ጀናዛውን ቀብረው ተበተኑ እኔ ብቻ ቀብሩ ጋ ቀረሁ አጠገቡም ቆሜ ዱአ ማድረግ ጀመርኩ።

"ያ ረብ ይህ እንግዳ ወደ አንተ መቷል እኔ የማላቀው ሆኖ እንግዳነት ወደኔ ቢመጣ በክብር አስተናግደው ነበር ታዲያ ወደ አንተ እክረመል አክረሚን(የለጋሶች ለጋስ) ሲመጣ እንዴት ትቀበለው ይሆን?"🤲🤲🤲

ከዛም ወጥቼ ወደ መስጅድ አመራሁ ጉዞ ስለነበረብኝ ትንሽ አረፍ አልኩ

በህልሜ ነጭ ልብስ የለበሰ ሰው አንተ ነህ ዱአ ያደረክልኝ ብሎ ጠየቀኝ?

እኔም አንተ ማነህ አልኩት??

"እኔ ቀብሬ ላይ ዱአ ያደረክልኝ ነኝ ወላህ አላህ ዱአህን ሰምቶ ይቅር አለኝ"♥♥

አላህ ከልባችው ዱአ ሚያደርጉ ሷሊህ ሰዎችን ይወፍቀን 🤲🤲

Sefa mohamad

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group