Translation is not possible.

የጋዛ እጅግ ትልቁና እድሜ ጠገቡ መስጅድ ዛሬ በእስራኤል የሚሳኤል ጥቃት ሙሉ ለሙሉ ወድሟል ።

ይህ መስጅድ ታላቁ የኡማሪ መስጅድ ወይንም ታላዉቁ የጋዛ መስጅድ በመባል ይታወቃል ! መስጅዱ ከሞንጎሎች ወረራ በፊት የተገነባ ነበረ ። ከዚያ ሞንጎሎች አፈራረሱት ግና መልሰው ማምሉኮች እጅግ አሳምረው ገነቡት ። ማምሉኮች መስጅዱን እንደገና የገነቡ በ1281 ከዛሬ 800 አመት በፊት ነበረ ።

ቱርኮቹ ማምሉኮች ከገነቡት በሗላ በርእደ መሬት አደጋ ፈረሰ ። በዚህ ጊዜ መስጅዱ እንደገና በኦቶማን ሱልጧኔት ተገነባ ።

ከዚያ በሗላ በሁለተኛው የአለም ጦርነት በእንግሊዝ የአየር ድብደባ መስጅዱ ተጎድቶ የነበረ ቢሆን እንደገና በሙስሊም ካውንስል ተጠግኖ የጋዛ ግዙፉና እድሜ ጠገቡ መስጅድ ሆኖ እስካሁን ቀጥሎ ነበር ።

ወራሪዋ እስራኤል ዛሬ ባደረሰቺው የአየር ሚሳኤል ጥቃት ግን መስጅዱ ሊወድም ችሏል ። ለሺህ ዘመናት የኖረው ታላቁ የሙስሊሞች የስነህንፃ ኩራት በወራሪዋ ሀገር አሜሪካ ሰራሽ ሚሳኤል ሲወድም በርግጥ እጅግ ልብ የሚሰብር ክስተት ሲሆን የዚህን ዘመን ሙስሊም ኡማ ሙትነትንም ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነው ።

image
image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group